Kishore Kumar Hits

Tekeste Getnet - Addis Neh lyrics

Artist: Tekeste Getnet

album: Deg Neh , Vol. 5


አወቅሁ ብዬ ደምድሜ ሳበቃ
ማለዳ ማለዳ አንተ አዲስ ነህ ለካ
ማለዳ ማለዳ አንተ አዲስ ነህ ለካ
እንደ ትናንትናው ከቶ አይደለህ
አንተ አትለመድም ዛሬም አዲስ ነህ
አዲስ ነህ ጌታ አዲስ ነህ
አዲስ ነህ ሁልጊዜ አዲስ ነህ
አዲስ ነህ ጌታ አዲስ ነህ
አዲስ ነህ ሁልጊዜ አዲስ ነህ
አለህ ብዙ ክብር አለህ ብዙ ኃይል
እንዲህ ነህ ብሎ ማን ገልጦህ ያውቃል
አረጀህ ተብሎ መርዶ አይነገር
ሁልጊዜ አዲስ ነህ አምላኬ ክበር
አለህ ብዙ ክብር አለህ ብዙ ኃይል
እንዲህ ነህ ብሎ ማን ገልጦህ ያውቃል
አረጀህ ተብሎ መርዶ አይነገር
ሁልጊዜ አዲስ ነህ አምላኬ ክበር
ትልቅ ነህ አንተ አትታወቅም
ለዘመንህ ቁጥር አይገኝም
የማቀውን ልናገር ብሞክር
በየዕለቱ አዲስ ነህ እግዚአብሔር
በየዕለቱ ሌላ ነህ እግዚአብሔር
ትልቅ ነህ አንተ አትታወቅም
ለዘመንህ ቁጥር አይገኝም
የማቀውን ልናገር ብሞክር
በየዕለቱ ሌላ ነህ እግዚአብሔር
በየዕለቱ አዲስ ነህ እግዚአብሔር
ፀሐይ ደካክማ ብርሃኗ ሲደበቅ
ለተረኛ ሥፍራዋን ስትለቅ
ደግሞ ሲገዛ ጨለማ እንደ ልቡ
ከታዛቸው ገብተው ፍጥረት ሲያሸልቡ
አንተ የማትተኛ የማታንቀላፋ
ትንሽ ልረፍ ሳትል ጨለማ እስኪጠፋ
ተረኛ መጥቶ ልቀቅ አይልህም
ተቀናቃኝ ሳይኖር ትገዛለህ ሁሌም
ትልቅ ነህ አንተ አትታወቅም
ለዘመንህ ቁጥር አይገኝም
የማቀውን ልናገር ብሞክር
በየዕለቱ አዲስ ነህ እግዚአብሔር
በየዕለቱ ሌላ ነህ እግዚአብሔር
ትልቅ ነህ አንተ አትታወቅም
ለዘመንህ ቁጥር አይገኝም
የማቀውን ልናገር ብሞክር
በየዕለቱ ሌላ ነህ እግዚአብሔር
በየዕለቱ አዲስ ነህ እግዚአብሔር

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists