Kishore Kumar Hits

Samuel Tesfamichael - Zinaw Yiwera lyrics

Artist: Samuel Tesfamichael

album: Melhike, Vol. 4


ዝናዉን ለሰማ እጅግ ያስፈራል
ባለ ዝና እንደሱ ከየት ይገኛል
በዘመናት መሃል ይታወቃል
ብቻውን የበላይ ሆኖ ይኖራል
ዝናዉን ለሰማ እጅግ ያስፈራል
ባለ ዝና እንደሱ ከየት ይገኛል
በዘመናት መሃል ይታወቃል
ብቻውን የበላይ ሆኖ ይኖራል
እግዚአብሔር (፰×)
እግዚአብሔርን ከእኔ ጋራ ታላቅ አርጉት ዝናዉ ይወራ
(እግዚአብሔርን ከእኔ ጋራ ታላቅ አርጉት ዝናዉ ይወራ) (፫×)
ይወራ ዝናው ይወራ (፪×)
በምድር ሁሉ ይወራ
ይወራ ዝናው ይወራ
ይወራ ዝናው ይወራ (፪×)
በአለም ሁሉ ይወራ
ይወራ ዝናው ይወራ
አንጎዳጎደ ልዑል ቃሉን ሰጠ
በክብሩ ሲቆም ምድሩን አናወጠ
የዘላለም ተራሮች ተፈረካከሱ
የጥንትም ኮረበቶች ወዲያዉ ፈራረሱ
ከሚንቦገቦገው ፀዳለ የተነሳ
ጽላቶች ከወጡበት ብርሃን የተነሳ
ጨረቃ እና ፀሐይ በቦታቸው ቆሙ
በክብሩ ነፅብራቅ እየተደመሙ
እየተደመሙ እየተደመሙ
በክብሩ ነፅብራቅ እየተደመሙ
እየተደመሙ እየተደመሙ
በክብሩ ነፅብራቅ እየተደመሙ
እየተደመሙ እየተደመሙ
እግዚአብሔር (፰×)
እግዚአብሔርን ከእኔ ጋራ ታላቅ አርጉት ዝናዉ ይወራ
(እግዚአብሔርን ከእኔ ጋራ ታላቅ አርጉት ዝናዉ ይወራ) (፫×)
ይወራ ዝናው ይወራ (፪×)
በምድር ሁሉ ይወራ
ይወራ ዝናው ይወራ
ይወራ ዝናው ይወራ (፪×)
በአለም ሁሉ ይወራ
ይወራ ዝናው ይወራ
ክብሩ ሰማያትን ሁሉ የሸፈነ
ስሙም በምድር የተመሰገነ
ለታላቅነቱ ፍፃሜ የሌለው
በዘመናት መሃል እርጅና ማያዉቀው
ክዋክብት ታዘዙ በህዋ አበሩ
በአፍንጫዉ እስትንፋስ ሙቆች ተከመሩ
ትልቅ ነህ የሚለው ቃል ፍፁም የማይገልፀዉ
እጅጉን ያስፈራል ዝናዉን እንደሰማው
ዝናዉን እንደሰማው (፬×)
እጅጉን ያስፈራል ዝናዉን እንደሰማው
ዝናዉን እንደሰማው
እግዚአብሔር (፰×)
እግዚአብሔርን ከእኔ ጋራ ታላቅ አርጉት ዝናዉ ይወራ
(እግዚአብሔርን ከእኔ ጋራ ታላቅ አርጉት ዝናዉ ይወራ) (፫×)
ይወራ ዝናው ይወራ (፪×)
በምድር ሁሉ ይወራ
ይወራ ዝናው ይወራ
ይወራ ዝናው ይወራ (፪×)
በአለም ሁሉ ይወራ
ይወራ ዝናው ይወራ
ይወራ ዝናው ይወራ
በአለም ሁሉ ይወራ
ይወራ ዝናው ይወራ
በአለም ሁሉ ይወራ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists