Kishore Kumar Hits

Samuel Tesfamichael - Edilegna lyrics

Artist: Samuel Tesfamichael

album: Melhike, Vol. 4


አንተ ባለህበት በከበረዉ ስፍራ
ከአንተ ጋራ ልሆን ስምህን እንድጠራ
እድሉን አገኘዉ በቤትህ ልቀድስ
እጥፍ ልስገድልህ ነፍሴን ፊትህ ላፍስስ
እንዴት መታደል ነው ስምህን መጥራቱ
ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ማለቱ
የተመረጠ ስም ከስም ሁሉ በላይ
አይኔን አድርጎታል ከአንተ በላይ እንዳላይ
የህይወቴ ኢየሱስ ጌታ ነህ ኢየሱስ
የኑሮዬ ኢየሱስ ንጉሥ ነህ ኢየሱስ
መአዛህ ኢየሱስ ስወደው ኢየሱስ
መገኘትህ ኢየሱስ ህይወቴ ነው
ኢየሱስ ኢየሱስ ወደድኩህ
ከእልፍ ከአእላፋት መረጥኩህ
ውዴ ከእንቁ ትበልጣለህ
ከማር ወለላ ይልቅ ጣፋጭ ነህ
አረ እንዴት እድለኛ ነኝ
በፊትህ ሞገስን አገኘሁኝ
የእኔ ብቻ አይበቃም ዝማሬ
ይገዛልህ ዘር ማንዘሬ
የቤትህ ስርዓት በሚደረግበት
ህዝቡም መላእክት ቅዱስ በሚሉበት
ዕድሉን አገኘሁ ዘላለም ላመልከው
ቅዱስ ቅዱስ እያልኩ ከቅዱሳን
እንዴት መታደል ነው ዘላለም ማምለኬ
ጎምበስ ቀና እያልኩ ፊትህ ተምበርክኬ
በማይነገር ክብር በሚደነቅ ብርሃን
ላይህ ጉዋጉችያለው ውዴ ኢየሱስ አንተን
ኢየሱስ ሙሽራዬ ኢየሱስ ቶሎ ና
ኢየሱስ መናፈቄ ኢየሱስ በዝቷልና
ኢየሱስ ማዶ ማዶ ኢየሱስ ማዶ እያየሁ
ኢየሱስ አማትሬ ኢየሱስ ጠብቅሃለው
ኢየሱስ ሙሽራዬ ኢየሱስ ቶሎ ና
ኢየሱስ መናፈቄ ኢየሱስ በዝቷልና
ኢየሱስ ማዶ ማዶ ኢየሱስ ማዶ እያየሁ
ኢየሱስ አማትሬ ኢየሱስ ጠብቅሃለው
ኢየሱስ ኢየሱስ ወደድኩህ
ከእልፍ ከአእላፋት መረጥኩህ
ዉዴ ከእንቁ ትበልጣለህ
ከማር ወለላ ይልቅ ጣፋጭ ነህ
አረ እንዴት እድለኛ ነኝ
በፊትህ ሞገስን አገኘሁኝ
የእኔ ብቻ አይበቃም ዝማሬ
ይገዛልህ ዘር ማንዘሬ
(ሙሽራዬ) ሙሽራዬ ኢየሱስ ቶሎ ና (ና ና ና)
ኢየሱስ መናፈቄ ኢየሱስ በዝቷልና
ኢየሱስ ማዶ ማዶ ኢየሱስ ማዶ እያየሁ
ኢየሱስ አማትሬ ኢየሱስ ጠብቅሃለው
(ሙሽራዬ) ሙሽራዬ ኢየሱስ ሆ ቶሎ ና
ኢየሱስ መናፈቄ ኢየሱስ በዝቷልና
ኢየሱስ ማዶ ማዶ ኢየሱስ ማዶ እያየሁ
ኢየሱስ አማትሬ ኢየሱስ ጠብቅሃለው
መንፈሱና ሙሽራያቱም ና ይላሉ
የሚሰማም ና ይበል
ማራናታ አሜን ጌታ ኢየሱስ ሆይ ቶሎ ና

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists