Kishore Kumar Hits

Samuel Tesfamichael - Timelekaleh lyrics

Artist: Samuel Tesfamichael

album: Melhike, Vol. 4


ገና ሰማይ እና ምድር ሳይፈጠር
ገና አማልዕክት የሚባል ሌላ ሳይኖር
ብቻህን በክብር ዙፋን ላይ ተቀመጠህ
ትመለካለህ (፮×)
ገና ፅሐይ ክዋክብት ሳይታሰቡ
ገና ንፋሳት ሳይወጡ ከመዛግቡ
በአእላፋት መላእክት ቀን ከሌት ተከበህ
ትመለካለህ (፮×)
ክብር የሚለው ቃል ሌላ ሳይከብርበት
አንተ ክብር ለብሰህ ዘላለም ኖርክበት
መክበር የሚለው ቃል ማንም ሳይከብርበት
አንተ ክብር ጠግበህ ዘላለም ኖርክበት
ክብር ማለት የሚያውቀው አንተን ነው
መጀመሪያ የታወቀዉ በአንተ ነው
ክበር እራሱ የሚያውቀው አንተን ነው
መጀመሪያ የታወቀዉ በአንተ ነው
ክበር እራሱ የሚያውቀው አንተን ነው
መጀመሪያ የታወቀዉ በአንተ ነው
ክብር ማለት የሚያውቀው አንተን ነው
መጀመሪያ የታወቀዉ በአንተ ነው
እናመልክሃለን እግዚአብሔር (፫×)

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists