Kishore Kumar Hits

Samuel Tesfamichael - Ameletech Nefse lyrics

Artist: Samuel Tesfamichael

album: Melhike, Vol. 4


እግዚአብሔር ባይራራልኝ
ልጁን ልኮ ባይታደገኝ
የጠላት ሴራ ወጥመድ ዘርግቶብኝ
የሙታን ሰፈር ሰው በቀረሁኝ
የጠላት ሴራ ወጥመድ ዘርግቶብኝ
የሙታን ሰፈር ሰው በቀረሁኝ
ግን አልተሳካም አልሆነለትም
ነፍሴን ከቶ አላገኛትም
በክርስቶስ በተሰራው ስራ
አመለጠች እንደ ወፍ በራ
አልተሳካም አልሆነለትም
ነፍሴን ከቶ አላገኛትም
በክርስቶስ በተሰራው ስራ
አመለጠች እንዴ ወፍ በራ
አመለጠች አመለጠች(፪×)
ነፍሴ እንደ ወፍ ከአዳኞች
ወጥመድ አመለጠች
አመለጠች አመለጠች(፪×)
ነፍሴ እንደ ወፍ ከአዳኞች
ወጥመድ አመለጠች
በራ በራ እንደ ወፍ በራ
በራ በራ እንደ ወፍ በራ
አመለጠች በራ (፪×)
በክርስቶስ ስራ
አመለጠች በራ
በመስቀል ላይ ስራ
አመለጠች በራ
አዳኙ በስዉር ወጥመድ አስቀመጠ
ከአሁን አሁን ያዘልኝ ሲል አይኑ እንዳፈጠጠ
አዳኘ ሲመጣ ወጥመዱ ሲረግጠዉ
ነፍሴን አስመልጦ ወጥመዱን ሰባበረዉ (፬×)
እንዲህ ነው ያመለጠችዉ ነብሴ (፪×)
እንደ ወፍ አመለጠች ነፍሴ (፪×)
በረረች ያመለጠችዉ ነብሴ (፪×)
በአዳኟ በእየሱሴ (፬×)
በእየሱሴ (፬×)
ሞት እና ሲኦል አንድ ላይ ተስማምተዉ
ዘላለሜን ሊያደርጉት በድቅድቅ ጨለማ
ሞት እና ሲኦል አንድ ላይ ተስማምተዉ
ዘላለሜን ሊያደርጉት በድቅድቅ ጨለማ
የትንሣኤዉ ጉልበት ሞትን ራሱን ገሎት
መዉጊያዉን ሰባብሮ ነብሴን አስመለጣት (፬×)
እንዲህ ነው ያመለጠችዉ ነብሴ (፪×)
እንደ ወፍ አመለጠች ነፍሴ (፪×)
በረረች ያመለጠችዉ ነብሴ (፪×)
በአዳኟ በእየሱሴ (፬×)
በእየሱሴ (፬×)

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists