Kishore Kumar Hits

Samuel Tesfamichael - Lyke Ende Kalihe lyrics

Artist: Samuel Tesfamichael

album: Yemigermegne Medane Newe, Vol. 1


ነፋሱ ቢነፍስ ወጀቡን ቢያጓራ
በበዛው ሠላምህ አለህ ከኔ ጋራ
አለም ብትነዋወጥ ማእበሉ ቢበዛ
ነፍሴ እርፍ አለች በፍቅርህ ተያዛ
የዘላለሜ ነህ ሁሉም ሲቀር ሗላ
መልህቅ የሆንከኝ ግራ እንዳልጋባ
መልህቄ
ያዝከኝ ኢየሱሴ
የፍቅርህ ሰንሰለት አጥብቆ ይዞኛል
እኔ ብደክምበት መቼ ይተወኛል
በሞት እታች ወርደህ መልህቅ የያዝከኝ
ልዩ ፍጥረት ቢሆን በሞት እንዳይለየኝ
የዘላለሜ ነህ ሁሉም ሲቀር ሗላ
መልህቅ የሆንከኝ ግራ እንዳልጋባ
መልህቄ
ያዝከኝ ኢየሱሴ
እንደ ነፍስ መልህቅ በሆነ ተስፋ
እርግጥ እና ፅኑ መቼም የማይጠፋ
በዚህኛው ቢሆን በወዲያኛው አለም
ጥብቅ አርገህ ያዝከኝ እስከ ለዘላለም
የዘላለሜ ነህ ሁሉም ሲቀር ሗላ
መልህቅ የሆንከኝ ግራ እንዳልጋባ
መልህቄ
ያዝከኝ ኢየሱሴ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists