Kishore Kumar Hits

Hanna Tekle - Yezelalem Fetari lyrics

Artist: Hanna Tekle

album: Yezelalem Fetari, Vol.2


እግዚአብሔር በይሁዳ የታወቅህ
ድንኳንህ በሳሌም ማደሪያህ በጽዮን
አንተ ብርሃን ተላብሰህ ደምቀህ
ግርማዊነትህ ከዘለዓለም ተራሮች ሁሉ ይልቃል
ልበ ሙሉ የሆኑት ሁሉ አለቁ
ከተግጻጽህ የተነሳ ፈረስና ፈረሰኛው
ጭልጥ ድብን ብለው ተኙ
የያዕቆብ አምላክ ሆይ
በአንተ ፊት ማንስ መቆም ይችላል
ማንስ መቆም ይችላል
መፈራት ያለብህ አንተ ብቻ
መወደስ ያለብህ አንተ ብቻ
እልሃለው ዛሬም እኔም ቆሜ
አንተው በሰጠኸኝ ዘመንና ቅኔ
ልዑል ሆይ ማደሪያህ ይባረክ
ቅዱስ ሥምህ ይባረክ
ልዑል ሆይ ማደሪያህ ይባረክ
ልዑል ሆይ ማደሪያህ ይባረክ
ልዑል ሆይ ማደሪያህ ይባረክ
ልዑል ሆይ ማደሪያህ ይባረክ
ከሀያላኑ በፊት ሀያል
ከብርቱዎቹ በፊት ብርቱ
የነበርህ አንተ ነህ የምትኖር አንተ ነህ
ፈጣሪያቸው አንተ ነህ ገዢያቸው አንተ ነህ
እግዚአብሔር አንተ ነህ አንተ ነህ
እነዚያ ዘመናቸው አልቆ ተረቱ
እንደ ቀልድ አባሩ አለፉ ተረሱ
ሲራቡ ሌላ ነገን ማየት
ባሉበት መዘግየት ከመሞት መሰንበት
አልቻሉም አልቻሉም
አለመሞት አልቻሉም
ነገን ማየት አልቻሉም
አልቻሉም አልቻሉም
ዝቅ ብዬ ሳይ አፈሩን
አልኩኝ አወይ አቤት አቤት
ስንት ጀግና ስንት ጐበዝ
ስንት አይደፈር ኖሯል በታች
ከምረግጠው መሬት
አሻቅቤ ሳይ ወደላይ ወደላይኛው ሠማይ
አየሁ የዘመን ልክ የዘመን ቁጥር
የዘመኑ ባለቤት የቁጥሩም ባለቤት
የሁሉን በላይ ሞትን የማያይ
መወደስ ያለበት እርሱ ብቻ
መመለክ ያለበት እርሱ ብቻ
እልሃለው እኔም ዛሬም እኔም ቆሜ
አንተ በሰጠኸኝ ዘመንና ቅኔ
ልዑል ሆይ ማደሪያህ ይባረክ
ቅዱስ ሥምህ ይባረክ
ማደሪያህ ይባረክ
ልዑል ሆይ ተባረክ
ዘለዓለምም ቢሆን የእርሱ ልክ አይደለም
መች በዚህ ይለካል የሠማይ የምድሩ የሁሉ ፈጣሪ
ኧረ እርሱ እንዲህ ነው ዘለዓለምን ፈጥሮ ወዶ በፈቃዱ
ዘለዓለምን ዘለዓለም ያኖረዋል እንጂ
ጭራሽ አይለካም እግዜሩ ክብሩ አይመዘንም
ክብሩ ለብቻው ነው ዝናው ለብቻው ነው
እስኪ አለው ይበለኝ አንድ ሥጋ ለባሽ
እንደ እግዚአብሔር ያለ እስኪ የትኛው ነው
የዘለዓለም ነዋሪ የዘለዓለም ፈጣሪ
የሁሉ በላይ ሞትን የማያይ
መወደስ ያለበት እርሱ ብቻ
መመለክ ያለበት እርሱ ብቻ
እልሃለው እኔም ዛሬም እኔም ቆሜ
አንተ በሰጠኸኝ ዘመንና ቅኔ
ልዑል ሆይ ማደሪያህ ይባረክ
ቅዱስ ሥምህ ይባረክ
ልዑል ሆይ ይባረክ
ልዑል ሆይ ይባረክ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists