Kishore Kumar Hits

Hanna Tekle - Weqt Endatabelash lyrics

Artist: Hanna Tekle

album: Yezelalem Fetari, Vol.2


ክረምት አልጠብቅም ክረምት ላይ ሆኜ
በጋን እኔ አልሻም በጋ ላይ ቁጭ ብዬ
እሰራለሁ አሁን ተራዬን አለቅም
ዘመኔ ላይ ቆሜ ዘመን አልጠብቅም
ጊዜዬ ነው
ወቅቴ ነው
ዘመኔ ነው
ተራዬ
እሰራለሁ እሮጣለሁ
በወቅቱ ዘርቼ ከሱ ጠብቃለሁ
ይረዳኛል አምናለሁ
የተሰጠኝ ጊዜዬ ነው
እሰራለሁ እሮጣለሁ
በወቅቱ ዘርቼ ከሱ ጠብቃለሁ
በጊዜ(×፬)
(Melody)
ትላንት ላልሆነለት ዛሬን አትንፈገው
ከንፈርህን መጠህ ሆዱን አታስብሰው
ተስፋ ለቆረጠው ምክር ካስፈለገ
ዐይኑን ግለጥና አድርሰው ለነገ
ትላንት ዛሬ አይደለም
ዛሬ ሌላ ቀን ነው
በትላንቱ በሬ ዛሬ ያረሰ ማነው
የመፅው ለፀደይ አይሆንም ወዳጄ
ወቅት እንዳታበላሽ ልንገርህ ማልጄ
በጊዜ(×፬)
አሁን የዋልንበት ነው ለነገ ተስፋ
የዘራነው ዘር ነው ሚጠብቀን ኋላ
ከሠራነው ዛሬን ከተጋን በብርቱ
እንደርሳለን ካልነው አይቀርም መድረሱ
በጊዜ(×፬)
ክረምት አልጠብቅም ክረምት ላይ ሆኜ
በጋን እኔ አልሻም በጋ ላይ ቁጭ ብዬ
እሰራለሁ አሁን ተራዬን አለቅም
ዘመኔ ላይ ቆሜ ዘመን አልጠብቅም
ጊዜዬ ነው
ወቅቴ ነው
ዘመኔ ነው
ተራዬ
እሰራለሁ እሮጣለሁ
በወቅቱ ዘርቼ ከሱ ጠብቃለሁ
ይረዳኛል አምናለሁ
የተሰጠኝ ጊዜዬ ነው
እሰራለሁ እሮጣለሁ
በወቅቱ ዘርቼ ከሱ ጠብቃለሁ
በጊዜ(×፬)

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists