Kishore Kumar Hits

Hanna Tekle - Zigabign lyrics

Artist: Hanna Tekle

album: Yezelalem Fetari, Vol.2


ልቤ ብዙ ብዙ ይመኛል
የአንተን ጥሎ ወዲያ ይሮጣል
አሳልፈህ አትስጠኝ ለራሴ
ባንተ ልኑር አልቁም በራሴ
ልቤ ብዙ ብዙ ይመኛል
የአንተን ጥሎ ወዲያ ይሮጣል
አሳልፈህ አትስጠኝ ለራሴ
ደርሶ አሳቢ ስሆን ለራሴ
እንደ ልብህ ልሁን እንደ ልብህ
እንደ ሃሳብህ ልኑር እንደ ፍቃድህ
እንደ ልብህ ልሁን እንደ ልብህ
እንደ ሃሳብህ ልኑር እንደ ፍቃድህ
ፍቃድህ በልቤ ላይ ትሁን
ትሰረኝ በራሴም አልሁን
ቀድመኸኝ ከወጣህ ከፊቴ
አልፈራም ብርቱ ነኝ አባቴ
ጥላህ ስር በምቾት አድራለው
ዘመኔን ባንተ ስር ካረከው
ፍቃድህ በልቤ ላይ ትሁን
ትሰረኝ በራሴም አልሁን
ቀድመኸኝ ከወጣህ ከፊቴ
አልፈራም ብርቱ ነኝ አባቴ
ጥላህ ስር በምቾት አድራለው
ዘመኔን ባንተ ስር ካረከው
የተከፈተ በር ሁሉ ካንተ አይደለም
ነግ ሊያጎድለኝ እንጂ ለመልካም አይደለም
ተደባልቆ የገባን ስኬቴ
አውጣልኝ ከቤቴ ከቤቴ
ሁሉ የሞላበት የሀሰት ገነት
ምን ሊበጅ ያላንተ አንተ የለህበት
ይሻል የለ ያንተው በረሃ
ሳላይ እህል ውሃ እህል ውሃ
ዝጋብኝ የስኬትን መንገድ
ካልሆነ ካልመጣ ከአንተ ዘንድ
የነገን እዳ እፈራለሁ
ሰግቼ ለምን እኖራለሁ
ይቅርብኝ የምቾቴ መንገድ
ካልሆነ ካልመጣ ከአንተ ዘንድ
የነገን ቁጣ እፈራለሁ
ሰግቼ ለምን እኖራለሁ
እንደ ልብህ ልሁን እንደ ልብህ
እንደ ሃሳብህ ልኑር እንደ ፍቃድህ
እንደ ልብህ ልሁን እንደ ልብህ
እንደ ሃሳብህ ልኑር እንደ ፍቃድህ
ያንተን ውድ ጊዜ መጠበቅ አቅቶኝ
የልብህን ሀሳብ መታገስ ተስኖኝ
የፈጠንኩ ሲመስለኝ ዘግይቼ
እንዳልገኝ ካየኸው ወርጄ
የእንጀራ ጩኸቴ ፅኑ ልመናዬ
በሞላልኝ ማግስት እንዳይሆን ገዳዬ
አንተ ያልከው ይሁን በህይወቴ
እኔ አልቅደም ቅደመኝ አባቴ
ዝጋብኝ የስኬትን መንገድ
ካልሆነ ካልመጣ ከአንተ ዘንድ
የነገን እዳ እፈራለሁ
ሰግቼ ለምን እኖራለሁ
ይቅርብኝ የምቾቴ መንገድ
ካልሆነ ካልመጣ ከአንተ ዘንድ
የነገን ቁጣ እፈራለሁ
ሰግቼ ለምን እኖራለሁ
እንደ ልብህ ልሁን እንደ ልብህ
እንደ ሃሳብህ ልኑር እንደ ፍቃድህ
እንደ ልብህ ልሁን እንደ ልብህ
እንደ ሃሳብህ ልኑር እንደ ፍቃድህ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists