Kishore Kumar Hits

Helina Dawit - YelibeGeta lyrics

Artist: Helina Dawit

album: YelibeGeta


የልቤ ጌታ የልቤ ጌታ የልቤ ጌታ የልቤ ጌታ
የልቤ ጌታ የልቤ ጌታ የልቤ ጌታ የልቤ ጌታ
ባይመስለኝም እንኳን ሁኔታዬ ጥቅጥቅ ያለ ቢሆን ጨለማዬ
ምርጫዬ መኖር ነው ደስ እያለኝ የማይሰማህ ችግር ስለሌለኝ
ማለዳ ነውና ሁሌ ላንተ አተወውም እና አቅም አተህ
ይሁን ብለህ ጠርተህ ባመጣኸው አቅም ችሎታህን አልገምተው
ባይመስለኝም እንኳን ሁኔታዬ ድቅድቅ ያለ ቢሆን ጨለማዬ
ምርጫዬ መኖር ነው ደስ እያለኝ የማያውቅህ ችግር ስለሌለኝ
ማለዳ ነውና ሁሌ ላንተ ሀሳብ አትቀይርም አቅም አተህ
ይሁን ብለህ ጠርተህ ባመጣኸው አቅም ችሎታህን አልገምተው
የልቤ ጌታ የልቤ ጌታ የልቤ ጌታ የልቤ ጌታ
የልቤ ጌታ የልቤ ጌታ የልቤ ጌታ የልቤ ጌታ
ብዙ ከሚያጋፉህ የሚያስታውቅ መንካት የነካውህ እኔ ነኝ
ብዙ ከሚጮሁት የዳዊት ልጅ ማረኝ ብዬ ያስቆምኩህ እኔ ነኝ
ብዙ ከሚሰሙህ ይበልጥ ያደመጥኩህ እኔ ነኝ
ብዙ ከሚቀርብህ የተጠጋጋውህ እኔ ነኝ
ወንድሜን ከሞት ቀስቅሰህ ላይቀር እንባዬን ማበስህ
ለምን ይሆን ሳለቅስ አይተህ ከኔ ጋር እንባህን ማፈሰስህ
ወንድሜን ከሞት ቀስቅሰህ ላይቀር እንባዬን ማበስህ
ለምን ይሆን ሳለቅስ አይተህ ከኔ ጋር እንባህን ማፈሰስህ
ስለምትወደኝ አይደል ወይ እንዳይከፋኝ ለዚያች አፍታ
ይነሳል ብለህ አልሳቅክም እየሱስ የልቤ ጌታ
ስለምትሳሳልኝ አይደል እንዳይከፋኝ ለዚያች አፍታ
በፍቅርህ እርገጠኛ ነኝ አንተ ነህ የልቤ ጌታ
ስቀበልህ እጄ ሳይሆን ልቤም አንድ ላይ ተነስቷል
ቀሚስህን ስነካ አይደል እምነቴ ቤቴ ተሰርቷል
ከመቅበዝበዝ ከመባከን ሀሳቤ እግርህ ስር መርጧል
ከምተሰጠኝ ነገር ይልቅ ልቤ ከቃልህ ተሰፍቷል
ከመንፈስህ ተወዳጅቷል
የልቤ ጌታ የልቤ ጌታ የልቤ ጌታ የልቤ ጌታ
የልቤ ጌታ የልቤ ጌታ የልቤ ጌታ የልቤ ጌታ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists