Kishore Kumar Hits

Helina Dawit - Tselote Ga lyrics

Artist: Helina Dawit

album: YelibeGeta


ላገኝህ ነው ደግሞ መሰለኝ ገና በፍለጋው ደስ አለኝ
ላገኝህ ነው ደግሞ መሰለኝ ገና በፍለጋው ረካሁኝ
ሽፍት ልበል ከግርግሩ ልራቅ ልረሳ
በእግሮችህ ስር መድሃኒትን ይዤ እንድነሳ
ከዛም ባለፈ ባንተ በራስህ እደነቃለው
ባውቅኩህ ቁጥር እወድህ እና እዛው ከርማለው
ጥፍት ልበል ከትርምሱ ልራቅ ልረሳ
በእግሮችህ ስር መድሃኒትን ይዤ እንድነሳ
ከዛም ባለፈ ባንተ በራስህ እደነቃለው
ባውቅኩህ ቁጥር እወድህ እና እዛው ከርማለው
አንተ ጋር የቆየ አንተን አንተን ይላል
የሰነባበተ ሌላ ሰው ይሆናል
ጠረንህን ለምዶት ከሩቅ ይለይሀል
በግርታው መሀል ጌታ እኮ ነው ይላል
በብዥታው መሀል እሱ አይደለም ይላል
አንተ ለካ አንተ ለካ ያለኸው ፀሎቴ ጋ
አንተ ለካ አንተ ለካ ያለኸው ጓዳዬ ጋ
ያለም ሁሉ ጥበብ ቢለካ በከንቱ ምጥ በፍለጋ ማን ሊጠጋህ
አንተ ለካ አንተ ለካ ያለኸው ፀሎቴ ጋ
ውዴ አንተ ለካ አንተ ለካ ያለኸው ጓዳዬ ጋ
ልብ ከፈለገ አንዴ ካሰበ መቼ ይረጋል
እንዳጣው ሲሰማው ከቀድሞ አብልጦ ይከተለዋል
በፍለጋ ውስጥ ልቡ ይዝላል ተስፋው ይደክማል
ሲያገኘው ደግሞ እናዳላዘነ ደስታው ይሞላል
የኔ ግን አንተን ፍለጋ ሲጨልም እና ሲነጋ
ገና እይፈለኩህ እንኳን አያለው ነፍሴ ስትረጋ ስትረጋጋ
የኔ ግን አንተን ፍለጋ ሲጨልም እና ሲነጋ
ገና እይፈለኩህ እንኳን አያለው ነፍሴ ስትረጋ ስትረጋጋ
አንተ ለካ አንተ ለካ ያለኀው ጉልበቴ ጋ
አንተ ለካ አንተ ለካ ያለኀው ጓዳዬ ጋ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists