Kishore Kumar Hits

Endale Woldegiorgis - Yan Aamet lyrics

Artist: Endale Woldegiorgis

album: Hyaw Minch


ያን ዓመት እያስታወስኩኝ
ያንን ወር እያስታወስኩኝ
ያንን ቀን እያስታወስኩኝ
ከአውሬው አፍ በአንተ እንደዳንኩኝ
አውቃለሁ ክብርን ምሥጋናን ለአንተ አመጣለሁ
አውቃለሁ ክብርን ምሥጋናን ለአንተ አመጣለሁ
አውቃለሁ ክብርን ምሥጋናን ለአንተ አመጣለሁ
አውቃለሁ ክብርን ምሥጋናን ለአንተ አመጣለሁ
ስንት መስከረም ስንት ጥቅምት
ከእባብ ከጊንጡ የዳንኩበት
ስንት ህዳር ነበር ስንት ታህሳስ
ከሞት ያዳንከኝ ደርሰህ ኢየሱስ
ስንት ጥር አልፏል ስንት የካቲት
ውይ አለቀልኝ ብዬ ያልኩበት
ስንት መጋቢት ስንት ሚያዚያ
ሃዘን ሲሆነኝ መውጫና መግቢያ
ግንቦትስ ሰኔ ሐምሌ ነሃሴ
የጭንቅን ቀን አይቷል ይህ ነፍሴ
በዚህ ሁሉ ግን ደርሰህ ያዳንከኝ
እንዳመሰግን ዛሬን ሰጠኸኝ
በዚህ ሁሉ ግን ደርሰህ ያዳንከኝ
እንዳመሰግን ዛሬን ሰጠኸኝ
በጠዋት በቀትር ባመሻሽ በሌሊት
ስራህን ለማሰብ ብራመድ የኋሊት
ትዝ የሚሉኝ ማስታውሳቸው
የአንተን ማዳን ያየሁባቸው
እኮ እነዚያ የሄዱት አርቦች
ሃሙስ ቅዳሜ ብዙ እሁዶች
እሮቦቼ ማክሰኞ ሰኞ
ያልፍኳቸው ማዳንህ ገኖ
ይሁኑልኝ ለመታሰቢያ
የአንተን ማዳን ሁሌ ለማውሪያ
እንዲህ ልበል ክበር ተመስገን
በአንተ ምህረት አለፈ ያ ቀን
አውቃለሁ ክብርን ምሥጋናን ለአንተ አመጣለሁ
አውቃለሁ ክብርን ምሥጋናን ለአንተ አመጣለሁ
አውቃለሁ ክብርን ምሥጋናን ለአንተ አመጣለሁ
አውቃለሁ ክብርን ምሥጋናን ለአንተ አመጣለሁ
በሌሊት ከእንቅልፌ በድንገት ስነቃ
ቀኑን ላለማየት እል ነበር ባልነጋ
ባልነጋ ስላልኩኝ መች ቀርቶ ሳይነጋ
ቀኑን እንዳዘንኩኝ እደርስ ነበር ምሽት ጋ
በብስቁልናዬ አዘንክልኝና
ለነፍሴ ሰጠሃት የመጽናናት መና
ሌሊቶቼም ሆኑ መዝሙር መቀበያ
ቀኖቼም የአንተን ፈቃድ ማገልገያ
አውቃለሁ ክብርን ምሥጋናን ለአንተ አመጣለሁ
አውቃለሁ ክብርን ምሥጋናን ለአንተ አመጣለሁ
አውቃለሁ ክብርን ምሥጋናን ለአንተ አመጣለሁ
አውቃለሁ ክብርን ምሥጋናን ለአንተ አመጣለሁ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists