Kishore Kumar Hits

Endale Woldegiorgis - Kidus lyrics

Artist: Endale Woldegiorgis

album: Hyaw Minch


እወድስሃለው በዜማ እወድስሃለው በቅኔ
እወድስሃለው በዜማ እወድስሃለው በቅኔ
የምስጋናዬ የአምልኮዬ መአዛ ይክበብህ
እንዲህ ነህ ብዬ በቃሌ አልገልጥህ
አምላኬ ልዩ ነህ
የምስጋናዬ የአምልኮዬ መአዛ ይክበብህ
እንዲህ ነህ ብዬ በቃሌ አልገልጥህ
አምላኬ ልዩ ነህ
አንተን ለማምለክ በመታደሌ የደስታዬ እንባ ከዓይኖቼ ይፈሳል
አጥንት ጅማቴ ቅዱስ እያሉ ልሳኔ ለአንተ ያቀነቅናል
እንደዘመርኩኝ እንደተቀኘሁ
እስከሰጠኸኝ እድሜ እኖራለሁ
ከኔ እስኪወሰድ ይህ እስትንፋሴ
ሳቀርብ እኖራለሁ ለስምህ ቅኔ ውዳሴ
ኦ ምንኛ መታደል ነው
ኦ ምንኛ መታደል ነው
እግዚአብሔር አምላክ ለሆንከው ሰው
እግዚአብሔር አምላክ ለሆንከው ሰው
ኢየሱሴ ጌታ ለሆንከው ሰው
ኢየሱሴ ጌታ ለሆንከው ሰው
ለስምህ ክብር እዘምራለሁ
ታላቅ ነህ ልልህ አፌን እከፍታለሁ
እስከምመጣ መንግስተ ሰማይ
እጅ አጣምሬ ቁጭ ብዬ አላይ
እዚሁ ማምለክ እጀምራለሁ
ለውሎዬ አንተን ቅዱስ እላለሁ
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ
ለቅድስናህ መታሰቢያ ምስጋና ፊትህ አቀርባለሁ
በኪሩቤል ላይ ለተቀመጥከው የሚገባህን ክብር አመጣለሁ
ምስጋናና ውበት በፊትህ ቅዱስነትና ግርማ በመቅደስህ
ሞልተውለሃል ተትረፍርፈው
እኔም አምልኮን እጨምራለሁ
ሞልተውለሃል ተትረፍርፈው
እኔም ምስጋናን እጨምራለሁ
ቅዱስነትህን አመልካለሁ አመልካለሁ
ሁሉን ቻይነትህን አመልካለሁ አመልካለሁ
አመልካለሁ አመልካለሁ አመልካለሁ አመልካለሁ
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists