Kishore Kumar Hits

Endale Woldegiorgis - Yebezegnal lyrics

Artist: Endale Woldegiorgis

album: Yebezegnal


ሰው ከሆነበት አስደንጋጭ ወሬ
ወየው ከሚያሰኝ ከክፉ ፈሬ
ሳልርበተበት ሳልል የት ልግባ
ከዓይኔ ሳይወጣ የሀዘን እንባ
ይቤዠኛል ያልኩት ይቤዠኛል
ያድነኛል ያልኩት ያድነኛል
ይቤዠኛል ያልኩት ይቤዠኛል
ያድነኛል ያልኩት ያድነኛል
ነፍሴ ማን አለና የቱን ለማን ስትልህ
ድንገት ስታጣቸው ቃል የገቡላትን
እጆቹን ዘርግቶ አቅፎ የተቀበላት
በጣር በጭንቋ ቀን አላት የሚቤዣት
ይቤዠኛል ያልኩት ይቤዠኛል
ያድነኛል ያልኩት ያድነኛል
ይቤዠኛል ያልኩት ይቤዠኛል
ያድነኛል ያልኩት ያድነኛል
እተርፋለሁ አላልቅም አብሬ
የሚያድነኝ ገብቷል በመንደሬ
የሚያድነኝ ገብቷል በሠፈሬ
ለሐጢያተኛው የሚመጣው ዱላ
የጻድቁን ቤት አይነካምና
የመንፈሱን ቤት አይነካምና
ሩትን ከተቤዣት ከቦዔዝ ሚበልጠው
ለተሻለው ኪዳን ለኔ ዋስ የሆነው
ልቤን የጣልኩበት ይህ ጌታ
በጭንቄ ደራሽ ነው የሚያስመካ
ልቤን የጣልኩበት ይህ ጌታ
በጭንቄ ደራሽ ነው የሚያስመካ
እተርፋለሁ አላልቅም አብሬ
የሚያድነኝ ገብቷል በመንደሬ
የሚያድነኝ ገብቷል በሠፈሬ
ለሐጢያተኛው የሚመጣው ዱላ
የጻድቁን ቤት አይነካምና
የመንፈሱን ቤት አይነካምና
ይቤዠኛል ያልኩት ይቤዠኛል
ያድነኛል ያልኩት ያድነኛል
ይቤዠኛል ያልኩት ይቤዠኛል
ያድነኛል ያልኩት ያድነኛል

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists