Kishore Kumar Hits

Kassa Tessema - Fano lyrics

Artist: Kassa Tessema

album: Fano (Ethiopian Contemporary Oldies Music


ፋኖ ፋኖ ፣ ኧረ ፋኖ ፋኖ
ኧረ ፋኖ ፋኖ
ተኩሶ ሲነጉድ ፣ የፈሪ ልምደኛ
ፊትለፊት ተጋዳይ ፣ ፋኖ እንደ መጋኛ
ኧረ ተው በሉት ፣ ያን ባለ ቡሎ
ሰጠው ለነፋስ ፣ አንጓሎ አንጓሎ ፣ አንጓሎ አንጓሎ
እንደ ቆላ ወፍ ፣ እንደ ግሪሳ
እንደ ቆላ ወፍ ፣ እንደ ግሪሳ
ያረፈው ልቤ ፣ ደግሞ ተነሳ ፣ ደግሞ ተነሳ
ፋኖ ፋኖ ፣ ፋኖ ፋኖ
ጋር ተልጦ ፣ ደግሞ አይላጥም
ቁርጥ አልሽልኝ ፣ እንደ ውሃ ጥም ፣እንደ ውሃ ጥም
ፋኖ ፋኖ
ሐረር ለኦጋዴን ፣ ምን ያህል ይርቃል
ትዝ ባልሽኝ ግዜ ፣ እንባዬ ይመጣል
እልም ያለው ጫካ ፣ እልም ያለው ዱር
ሲነጋገር ያድራል ፣ ከመውዚሩ ጋር ፣ ከመውዚሩ ጋር
እንኳን ባልንጀራ ፣ ልብ አይታመንም
ፋኖ ፋኖ ፣ ፋኖ ፋኖ
ኧረ ፋኖ ፋኖ
ፋኖ ሀገሩ ገባ ፣ ሳይሰናበተኝ
ያ ጀግና ወታደር ፣ ሰውም አያደርገኝ
ሰውም አያደርገኝ
ፋኖ ፋኖ ፣ ፋኖ ፋኖ
እበላው በርጭቃ ፣ ልኳንዳው ምን ሆኖ
የልቤ አስታማሚ ፣ ና ፋኖ ና ፋኖ ፣ ና ፋኖ ና ፋኖ
ሆ ሆ
ተው ሳበው ሳበው
ሳበው መሸብህ ፣ ሳበው መሸብህ
የጆቢራ እራት ፣ ግብር አለብህ
ግብር አለብህ ፣ ግብር አለብህ
ፋኖ ፋኖ
የወንድ ልጅ እናት ፣ ታጠቂ በገመድ
የወንድ ልጅ እናት ፣ ታጠቂ በገመድ
ልጅሽን አሞራ እንጂ ፣ አይቀብረውም ዘመድ
አይቀብረውም ዘመድ
ፋኖ ፋኖ ፣ ፋኖ ፋኖ
ከባልንጀራው ፣ ማታ የተለየ
ከባልንጀራው ፣ ማታ የተለየ
እንደ አጥቢያ ኮኮብ ፣ ሲነጋ ታየ ፣ ሲነጋ ታየ
ፋኖ ፋኖ
ኧረ ተው በሉት
ኧረ ተው በሉት ፣ ያን ባለ ቡሎ
ሰጠው ለነፋስ ፣ አንጓሎ አንጓሎ ፣ አንጓሎ አንጓሎ
ፋኖ ፋኖ
ፋኖ ፋኖ አለችኝ ፣ ፍንን ያርጋትና ፣ ፍንን ያርጋትና
ግንድ አልብሱ መጣ ፣ ማለቷ ቀረና ፣ ማለቷ ቀረና
ፋኖ ፋኖ ፣ ፋኖ ፋኖ
የምር ተኳሹን ፣ እኛ ስናውቀው
ዝናር በእቅፌን ፣ ማን ደባለቀው ፣ ማን ደባለቀው
ፋኖ ፋኖ ፣ ፋኖ ፋኖ ፣ ፋኖ ፋኖ
ወዘት በይ ልቤ ፣ እንደ ጀበና ፣ እንደ ጀበና
አልወጣልሽም ፣ የጦር ባፈና ፣ የጦር ባፈና
የጦር ባፈና ፣ የጦር ባፈና

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists