የአምባሰል ማር ቆራጭ
ይወጣል በገመድ
አደራ ቢያስቀምጥ
ይበላል ወይ
ዘመድ ይበላል ወይ
የአምባሰል ተሟጋች
አያውቅም ይግባኝ
በድህነቴ ላይ አንቺን ጣለብኝ
አንቺን ጣለብኝ
ጋይቼዉ ባይበቃኝ
ዉስጥ አንጀቴ ከስሎ
ቅስሜን ሰብሮት ነበር ፍቅር ላንቺ ብሎ
ፍቅር ላንቺ ብሎ
እንዴት ራስ አጣሽ እኔን መመልከቻ
ስሜ ባንቺ ጠፍቶ ሲሆን መተረቻ
ሲሆን መተረቻ ሲሆን መተረቻ
በገፍ እኔን እል ነበር ውስጥ አካሌን ገልቦ
ያለቦታዉ ሲሄድ እግሬ ተቅለብልቦ
ልቤ በመጨከን ሀሳብሽን ገምቶ
ደና ዋይ ይልሻል ካንቺ ተለይቶ
ላኳት ታስሪያለሁ በፍቅሯ ሰንሰለት
መሞቴ ነዉና አትመጣም ያሉኝ እለት
እሷን ያጣሁ ለታ ተጋድሜ በአልጋ
በእህህ ብቻ ነዉ ሌቱን የማነጋ
እንጀራም አልበላ ውሀንም አልጠጣ
ቁርስ እራት ምሳዬ እሷ ሳትመጣ እሷ ሳትመጣ
እንደ አላማ ሰንደቅ የወጣች በጠዋት
መጨነቅ በዛብኝ ቀን ከፊቴ ሳጣት
ቀን ከፊቴ ሳጣት
ዐይንን ጥሩ ብንል ጥርስ መንጣቱ ምነዉ
ዐይንን ጥሩ ብንል ጥርስ መንጣቱ ምነዉ
ሽንጧ ገላመጠን ከቶ ምን አረግነው
ከቶ ምን አረግነው ከቶ ምን አረግነው
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist