ኦሆሆ...
ኦሆሆ...
እዬዬም አትበሉ እንዳውም???
ሳውቀው ገብቻለው ዘመድ ሲመክርሽ
ትዝታህን ውሰድ ብለሽ የላክሽብኝ አንቺው ጋር ይቀመጥ
እኔም ያንቺ አለብኝ ×2
አንች ቀጣፊ ዋሾ እኔም አወኩብሽ
ወይ ከኔ ወይ ከርሱ አይሆንም ወይ ልብሽ
ሙቺም እንዳልልሽ ታናድጃለሽ
ኑሪም እንዳልልሽ ታናድጃለሽ
ሙቺም እንዳልልሽ ታዛዝኛለሽ
ሰወች ተኝተው አንቺ ተቀምጠሽ
እህህ የሚያሰኝ በሽታ ይስጥሽ
እስቲ በስመአብ በሉ እንስማ ታምር
ቤቷን አሰርታ እመንገዴ ስር
ኤጭ አለ ውበቷ እንደ እንግሊዝ ባቡር
ደጋፊው ሻንቅላ የመሰለ ዱር
አይኗ ቃታ ገብቶ ጀግና ሚያባርር
እንደ አዲስ መትረየስ ከሩቅ የሚጥል
ቢያነቡት አያልቅም የሷን ታምራት
ኮራ ብሎ ዳሌ እጥፍ ብሎ አንጀት
ልብ ይነጠፍ ይሆን እመደቡ ላይ
ምን ይነጠፍ ይሆን እመደቡ ላይ
አንድነት ቢኖረን እሱም ጠፋ ወይ
እሱም ጠፋ ወይ እሱም ጠፋ ወይ
???? ልጅ መሆንሽን አውቃለሁ
እኔ እምነቴን ይዤ እጠብቅሻለሁ
እኔ እምነቴን ይዤ እጠብቅሻለሁ
አይንን ጥሩ ብንል ጥርስ መንጣቱ ምነው
አይንን ጥሩ ብንል ጥርስ መንጣቱ ምነው
ሽንጧ ገላመጠን ከቶ ምን አረግነው
ሽንጧ ገላመጠን ከቶ ምን አረግነው
ጎበዝ እና ፈሪ ሁለት መልክ ይዘሽ
ጎበዝ እና ፈሪ ሁለት መልክ ይዘሽ
ጥርስሽ ሰው ገደለ ከንፈርሽ ሲሸሽ
ጥርስሽ ሰው ገደለ ከንፈርሽ ሲሸሽ
ከንፈርሽ ሲሸሽ ከንፈርሽ ሲሸሽ
ወረቀቱ ከኔ ይድረሱ ካንቺ ነዉ
ወረቀቱ ከኔ ይድረሱ ካንቺ ነዉ
ልቤ መናፈቁን አልተወም ገና ነዉ
መሸ ደና እደሩ ተቀረ ልማዴ
መሸ ደና እደሩ ተቀረ ልማዴ
ተከፍቶ ማደሩን አይወደውም ሆዴ
እንኳን አንቺንና የምወድሽን
እንኳን አንቺንና የምወድሽን
ሳየው እፈርሳለው ፎቶግራፍሽን
ሳየው እፈርሳለው ፎቶግራፍሽን
በአለም የሚንሳፈፍ ትዝታሽ ንፋስ ነዉ
በአለም የሚንሳፈፍ ትዝታሽ ንፋስ ነዉ
አንድ ሰው በሆዱ በአፉ ይዞ ማይችለው
ልተውሽ እልና ሳስብ ወደሌላ
ሳስብ ወደሌላ ሳስብ ወደሌላ
ይመጣል ትዝታሽ ደቂቃ ሳይሞላ
ሰርቼ እንዳልበላ በተቻለኝ አቅሜ
በትዝታሽ ይሆናል የምውለው ቆሜ
በትዝታሽ ይሆናል የምውለው ቆሜ
አዲስ ልብስ በወረት በጣም ይወደዳል
አዲስ ልብስ በወረት በጣም ይወደዳል
ግን ማለቂያው ሲደርስ ሲያጥቡት ይቀደዳል
ትኩሱን ካልሆነ ቡና እና ፍቅር
ትኩሱን ካልሆነ ቡና እና ፍቅር
የቀዘቀዘ እንደሆነ አያድርስ ሲመር
አያድርስ ሲመር አያድርስ ሲመር
እህህ ማለቷ መታመሟ እንዲ ነዉ
እስቲ ጠይቁልኝ ምኗን ነዉ
ምኗን ነዉ ምኗን ነዉ
ከፋሽ ወይ ደስ አለሽ ስታጪኝ ካገሩ
ፍቅር ይከፈላል ከዋሉ ካደሩ
መንታ መንገድ ላይ ልቤ መንታ ሆኖ
መለየት አይቀርም ሰውና ሰው ሆኖ
መለየት አይቀርም ሰውና ሰው ሆኖ
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist