Kishore Kumar Hits

Yirdaw Tenawe - Befekrish Teyizo lyrics

Artist: Yirdaw Tenawe

album: Jenber


በፍቅርሽ ተይዞ ልቤ ደጅ ይጠናል
እንድታናግሪው ፈልጎም ይሆናል
በፍቅርሽ ተይዞ ልቤ ደጅ ይጠናል
እንድታናግሪው ፈልጎም ይሆናል

እዩት እዚያ ማዶ ከገደሉ ስር
ጠይም ልጅ ይፈልቃል ውሀ ይመስል
እናት አልረገመኝ አባት አልረገመኝ
ብቻዬን መኝታ ምነው ደጋገመኝ

በፍቅርሽ ተይዞ ልቤ ደጅ ይጠናል
እንድታናግሪው ፈልጎም ይሆናል
በፍቅርሽ ተይዞ ልቤ ደጅ ይጠናል
እንድታናግሪው ፈልጎም ይሆናል

ተዋት ተዋት አሉኝ ጎረቤቱ ሁሉ
እንደኔ መች አዩት ሰውነትሽን ሁሉ
አልጋው አንቺን ለምዶ ትራሱ አንቺን ለምዶ
ይቀሰቅሰኛል ለሊት እንደመርዶ

በፍቅርሽ ተይዞ ልቤ ደጅ ይጠናል
እንድታናግሪው ፈልጎም ይሆናል
በፍቅርሽ ተይዞ ልቤ ደጅ ይጠናል
እንድታናግሪው ፈልጎም ይሆናል

ወረቀቱ ከኔው ፀሀፊው ሳይቸግረኝ
ነገር ወዲያ ወዲህ ሆነና ቸገረኝ
ምን ያደርጋል ፖስታ ነጋዴ ቢያመጣው
መገናኘት ነበር ናፍቆት የሚያወጣው

በፍቅርሽ ተይዞ ልቤ ደጅ ይጠናል
እንድታናግሪው ፈልጎም ይሆናል
በፍቅርሽ ተይዞ ልቤ ደጅ ይጠናል
እንድታናግሪው ፈልጎም ይሆናል

ተዋት ተዋት አሉኝ ጎረቤቱ ሁሉ
እንደኔ መች አዩ ሰውነትሽን ሁሉ
አልጋው አንቺን ለምዶ ትራሱ አንቺን ለምዶ
ይቀሰቅሰኛል ለሊት እንደመርዶ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists