Kishore Kumar Hits

Yirdaw Tenawe - Jenber lyrics

Artist: Yirdaw Tenawe

album: Jenber


አልገለጥ አለ ተጋርዶ ሰፈሯ
ቀረች ከህዋው ላይ ከጠረፍ ድንበሯ
ምን ይሆን የፀሐይ ማፈሯ
ምን ይሆን የጀምበር ማፈሯ
ምን ይሆን የፀሐይ ማፈሯ
ምን ይሆን የጀምበር ማፈሯ
አልገለጥ አለ ተጋርዶ ሰፈሯ
ቀረች ከህዋው ላይ ከጠረፍ ድንበሯ
ምን ይሆን የፀሐይ ማፈሯ
ምን ይሆን የጀምበር ማፈሯ
ምን ይሆን የፀሐይ ማፈሯ
ምን ይሆን የጀምበር ማፈሯ

ነይ ፀሐይ የአድማስ መጋረጃሽ ፀሐይ
በሽንፈት ሲከለል
ነይ ፀሐይ አንቺን ለመሰወር ፀሐይ
ዳመናው ሲቆለል
ነይ ፀሐይ ጠፈሩን ባልዳኘው ፀሐይ
ህዋው ባይከሰስ
ነይ ፀሐይ እጠብቅሻለሁ ፀሐይ
ያንቺም ቀን እስኪደርስ
የንጋት የጠዋት ሙቀቴን
አስጥላኝ የምሽት መብራቴን
እንደምን ልቁረሰው እራቴን
አላውቀው ጓዳዬን ማጀቴን
የንጋት የጠዋት ሙቀቴን
አስጥላኝ የምሽት መብራቴን
እንደምን ልቁረሰው እራቴን
አላውቀው ጓዳዬን ማጀቴን

አልገለጥ አለ ተጋርዶ ሰፈሯ
ቀረች ከህዋው ላይ ከጠረፍ ድንበሯ
ምን ይሆን የፀሐይ ማፈሯ
ምን ይሆን የጀምበር ማፈሯ
ምን ይሆን የፀሐይ ማፈሯ
ምን ይሆን የጀምበር ማፈሯ
ነይ ፀሐይ ከሰው ተደብቀሽ ወዴት
ለማን ልትበጂ
ነይ ፀሐይ ያንቺማ መገለጥ ፀሐይ
ለኔ ነበር እንጂ
ነይ ፀሐይ ጠፈሩን ባልዳኘው ፀሐይ
ህዋው ባይከሰስ
ነይ ፀሐይ እጠብቅሻለሁ ፀሐይ
ያንቺም ቀን እስኪደርስ
እምቁን ግለጪው አውጥተሽ
ጨለማን በብርሃን ተክተሽ
አጫውቺኝ በይ እንዳስለመድሺኝ
በኩርፊያ ጭጋግ አታልብሺኝ
እምቁን ግለጪው አውጥተሽ
ጨለማን በብርሃን ተክተሽ
አጫውቺኝ በይ እንዳስለመድሺኝ
በኩርፊያ ጭጋግ አታልብሺኝ

አልገለጥ አለ ተጋርዶ ሰፈሯ
ቀረች ከህዋው ላይ ከጠረፍ ድንበሯ
ምን ይሆን የፀሐይ ማፈሯ
ምን ይሆን የጀምበር ማፈሯ
ምን ይሆን የፀሐይ ማፈሯ
ምን ይሆን የጀምበር ማፈሯ

ነይ ፀሐይ የአድማስ መጋረጃሽ ፀሐይ
በሽንፈት ሲከለል
ነይ ፀሐይ አንቺን ለመሰወር ፀሐይ
ዳመናው ሲቆለል
ነይ ፀሐይ ጠፈሩን ባልዳኘው ፀሐይ
ህዋው ባይከሰስ
ነይ ፀሐይ እጠብቅሻለሁ ፀሐይ
ያንቺም ቀን እስኪደርስ
የንጋት የጠዋት ሙቀቴን
አስጥላኝ የምሽት መብራቴን
እንደምን ልቁረሰው እራቴን
አላውቀው ጓዳዬን ማጀቴን
እምቁን ግለጪው አውጥተሽ
ጨለማን በብርሃን ተክተሽ
አጫውቺኝ በይ እንዳስለመድሺኝ
በኩርፊያ ጭጋግ አታልብሺኝ
የንጋት የጠዋት ሙቀቴን
አስጥላኝ የምሽት መብራቴን
እንደምን ልቁረሰው እራቴን
አላውቀው ጓዳዬን ማጀቴን
እምቁን ግለጪው አውጥተሽ
ጨለማን በብርሃን ተክተሽ
አጫውቺኝ በይ እንዳስለመድሺኝ
በኩርፊያ ጭጋግ አታልብሺኝ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists