Kishore Kumar Hits

Aregahegn Worash - Yafekeresh Libbe lyrics

Artist: Aregahegn Worash

album: Beka Beka


ያፈቀረሽ አይኔ አሻግሮ ያይሻል
የናፈቀሽ ልቤ ሲያስብሽ ያመሻል
አሃሃ አይ ውበት አሃሃ አይ ቁመና ሁሉን አድሎሻል
አሃሃ ያም ለኔ አሃሃ ያም የኔ እንዴት ይሻልሻል
ያፈቀረሽ አይኔ አሻግሮ ያይሻል
የናፈቀሽ ልቤ ሲያስብሽ ያመሻል
አሃሃ አይ ውበት አሃሃ አይ ቁመና ሁሉን አድሎሻል
አሃሃ ያም ለኔ አሃሃ ያም የኔ እንዴት ይሻልሻል

ወይ ንግግር አላውቅ አንደበቴም ዝግ ነው
የቀዬው ጎረምሣ አንቺን አሳቢ ነው
ከብቶቼን ለግጦሽ እነዳለሁ
ወንዙ ዳር ተቀምጠሽ አይሻለሁ
እንዴት ቀርብሻለሁ

እንስራሺን ያዢና አንቺ ሰው
እዋርካው ስር ላግኝሽ
ልቤን አረጋግቼ ያገር ልጅ
የሆዴን ላነጋግርሽ
ቤትሽ ከጎኔ ሆኖ አንቺ ሰው
በዚህ ላይ አብሮ አደጌ
አንገቴ ዘሞ ዋለ ያገር ልጅ
ላውጋሽ እንዴት አድርጌ
ኧረ እኔማ አዘንኩኝ በራሴው ተፈጥሮ
ባላወኩሽ ኖሮ
እዘኚልኝ አፍቅሬሽ ተጎዳው በጣሙን
ኧረ እንደምን ልሁን
ኧረ እኔማ አዘንኩኝ በራሴው ተፈጥሮ
ባላወኩሽ ኖሮ
እዘኚልኝ አፍቅሬሽ ተጎዳው በጣሙን
ኧረ እንደምን ልሁን

ያፈቀረሽ አይኔ አሻግሮ ያይሻል
የናፈቀሽ ልቤ ሲያስብሽ ያመሻል
አሃሃ አይ ውበት አሃሃ አይ ቁመና ሁሉን አድሎሻል
አሃሃ ያም ለኔ አሃሃ ያም የኔ እንዴት ይሻልሻል
ያፈቀረሽ አይኔ አሻግሮ ያይሻል
የናፈቀሽ ልቤ ሲያስብሽ ያመሻል
አሃሃ አይ ውበት አሃሃ አይ ቁመና ሁሉን አድሎሻል
አሃሃ ያም ለኔ አሃሃ ያም የኔ እንዴት ይሻልሻል

አወይ የቃል ችግር የስትንፋሴ ድክመት
ስሜቴን ላብራራው ከራሴው ስሟገት
ጀንበሯም ጠለቀች ቀኑም መሸ
አወይ የኔ ድካም ተበላሸ
ድፍረት ከኔ ሸሸ

የአንባ ውብ መሆንሽን አንቺ ሰው
ሁሉም ያወጋልኛል
መቀደሜንም ሰጋሁ ያገር ልጅ
ኧረ እንዴት ይሻለኛል?
የመስኩ ውሏችንማ አንቺ ሰው
ምንኛ ወደድኩልሽ
ላንድ ቀን ቀርተሽ እንደው
ያገር ልጅ የወር ነው የምናፍቅሽ
ምን ተሻለኝ አልቻልኩም ልነግርሽ ያሳቤን
የሆዴን የልቤን
አብሮ ማደግ በእህትነትማ ከቀረ
ለምን ተፈቀረ?
ምን ተሻለኝ አልቻልኩም ልነግርሽ ያሳቤን
የሆዴን የልቤን
አብሮ ማደግ በእህትነትማ ከቀረ
ለምን ተፈቀረ?
ኧረ እኔማ አዘንኩኝ በራሴው ተፈጥሮ
ባላወኩሽ ኖሮ
እዘኚልኝ አፍቅሬሽ ተጎዳው በጣሙን
ኧረ እንደምን ልሁን?
ኧረ እኔማ አዘንኩኝ በራሴው ተፈጥሮ
ባላወኩሽ ኖሮ
እዘኚልኝ አፍቅሬሽ ተጎዳው በጣሙን
ኧረ እንደምን ልሁን?

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists