Kishore Kumar Hits

Sayat Demissie - Min Teshalew lyrics

Artist: Sayat Demissie

album: Kihe 3, Vol. 1


ነገሮችን ማግኘት የማይሞላው
መወደድ እርካታ ያልሰጠው
እውነታውን በሽሽት ላይ ላለው
ተቸጋሪ ልቤን ምን ተሻለው
ከጊዜ ተጣልቼ ህልሜን እይዘውና
መተኪያ እፈልጋለሁ ቶሎ ጣዕሙ ያልቅና
ደግሞ ሌላ ሩጫ ሌላ ተራራ መውጣት
በቃኝ የማይለውን ፍላጎትን ለመሙላት
መንገዱ ሩቅ ነው መዳረሻው
ሁሌ አዲስ ነገር ለሚያሰኘው
ስግብግብ ልቤን ስሜቴ አስሮት
ምናለ ባረፍኩ ደስታን አስተምሮት
በተሰጠኝ ባገኘሁት መርካትም በቻልኩ
ባወቅኩበት ባወቅኩበት ባወቅኩበት
በተሰጠኝ ባገኘሁት መርካትም በቻልኩ
ባወቅኩበት ባወቅኩበት ባወቅኩበት
ነገሮችን ማግኘት የማይሞላው
መወደድ እርካታ ያልሰጠው
እውነታውን በሽሽት ላይ ላለው
ተቸጋሪ ልቤን ምን ተሻለው
እረፍት የለኝም ውስጤ ሃሳብ ይሞግተኛል
ያለኝ በቂ እንዳልሆነ እያሰብኩ ይደክመኛል
እንደገና አዲስ ቤት አዲስ ስም አበጃለሁ
ራሴን ለብቻዬ መጋፈጥ እየፈራሁ
መንገዱ ራቀኝ የምረካበት
ስራ ከፈታሁ ከታሰርኩበት
ስግብግብ ልቤን ስሜቴ አስሮት
ምናለ ባረፍኩ ደስታን አስተምሮት
በተሰጠኝ ባገኘሁት መርካትም በቻልኩ
ባወቅኩበት ባወቅኩበት ባወቅኩበት
በተሰጠኝ ባገኘሁት መርካትም በቻልኩ
ባወቅኩበት ባወቅኩበት ባወቅኩበት
በተሰጠኝ ባገኘሁት መርካትም በቻልኩ
ባወቅኩበት ባወቅኩበት ባወቅኩበት
በተሰጠኝ ባገኘሁት መርካትም በቻልኩ
ባወቅኩበት ባወቅኩበት ባወቅኩበት

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists