Kishore Kumar Hits

aschalew fetene - Enatiwa Gonder lyrics

Artist: aschalew fetene

album: Enatiwa Gonder


በባልቴት ውበት ሁሌም ወይዘሪት
ማይነጥፍ ጅረት ጎህ ለነፃነት
ፈጣሪ ጦቢያን ሲከልላት
የምሰሶዋን ስም ጎንደር አላት
እንዳለች አለች ታተይ ሙሽሪት
ሒያጅና መጭን እንደታዘበች አዬ አዬ አዬ
ኧረ ዳማይ ዳማይ
ኧረ ዳማይ ዳማይ
ኧረ ዳማይ ዳማይ
ኧረ ዳማይ ዳማይ
እስኪ እህህ ልበል ጥቂት ባንች ቦታ
ታንጀትሽ ላይ ሆኘ ኸልብሽ በአንድ አፍታ
እንዴት ነው አዘዞ ጮማ በልቶ ጠጅ
ታንች የሚያደርሰኝ መግደርደርሽ እንጅ
የአባት የማረጉን ወግ ወጉን አዳብላ
አሳድጋኛለች እሹሩሩ ብላ
የምድር መዳኛው ታጠነ አርባራቱ
መሥዋአት አቅርቡ ስለት ለታቦቱ
እናትዋ ጎንደር ትንፋሽዋ ጎንደር
እህልዋ ጎንደር አካልዋ ጎንደር
ኧረ በፈጠረህ ኧረ እንዴው በሞቴ
እስኪ ተወኝ ባክህ ላታፅናናኝ እቴ
ይልቅስ ውሰደኝ ካለበት እትብቴ
መፅናኛየ እሷ ናት ልሒድ ወደ እናቴ
እናትዋ ጎንደር
እሽሩሩ ጎንደር
ኧረ ኧረ ጎንደር
ትንፋሽዋ ጎንደር
የዋልያ ቀንዱን መሥሎ ሹርባዋ
ሰልመም ብላ መጣች ኧረግ እናትዋ
ልቧም ካልፈቀደ ደስም ካላላት
በካሳ አትጨክንም በፋሲል በላት
በጎንደሮች መዳፍ ስጎርስ እዛም እዛም
ተመልሼ መጣሁ በእጄም ሳልጠቀም
ክፋ እስለምደሽኝ ጮማና ወርች
እናና ተጎዳሁ እኔ ስርቅ ካንች
እናትዋ ጎንደር
ትዝታዋ ጎንደር
ትንፋሽዋ ጎንደር
አካልዋ ጎንደር
ተይ ደሜ ተይ ደሜ
ተይ ደማም ተይ ደማም
የበሽታን ነገር ለሐኪም ይሰጡታል
የአጋንንትን ነገር ጠበል ይገቡታል
የጎንደርን ናፍቆት እንዴት ያረጉታል
እነቴቴ ጉርሻ ኧረ እንደምናችሁ
እነዋዋ ጉርሻ ኧረ እንደምናችሁ
ጉብ ጉብ አለብኝ አፈር ልብላላችሁ
የመሣፍንቱ እናት እቴቴ ማንአህሎሽ
ጉድ ጉድ በይልኝ ጥምቀት መጣሁልሽ
ተይ ደሜ ተይ ደሜ
ተይ ደማም ተይ ደማም
እንደ ህማማቱ የአንችው ፆመኛሽ
በባዶ እግሬ እምብርክክ የምሳለምሽ
ተይ ደማም ተይ ደማም
ተይ ደሜ ተይ ደሜ
ተይ ደማም ተይ ደማም
መሠንቆ ተናገር ጀግንነቱን አውራ
አርግፎ የሚጥል ተሰማይ አሞራ
ድንበር ጠባቂ ነው በጠላቱ አይሞትም
መሣሪያው ደም መላሽ እንደ ታናሽ ወንድም
ተይ ደሜ ተይ ደሜ
ተይ ደማም ተይ ደማም
ኧረ ጀግኔ ጀግኔ
ተይ ደማም ደማም
ኧረ ጎንደር ጎንደር
እንስፍስፏ ጎንደር
አካልዋ ጎንደር
ተይ ደማም ደማም
ተይ ደማም ተይ ደማም
ኧረረረረረረ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists