Kishore Kumar Hits

Abebe Teka - Agerwa Wedia Mado lyrics

Artist: Abebe Teka

album: Wefitu


በመንታ ጡቶቻ መሃል ተጋድሜ
በጥርሷ ዘበኛ በከንፈር ታድሜ
ስነቃ ባዶ ቤት ናፍቆት ተሸልሜ
ላላገኛት ነውወይ ላይፈታ ህልሜ
ላላገኛት ነውወይ ይሄሁሉ ህልሜ
በጥርሷ ዘበኛ በከንፈር ተድሜ
ጡቶቻ መሃል ስኖር ተጋድሜ
ስነቃ ባዶ ቤት ናፍቆት ተሸልሜ
ላላገኛት ነውወይ ላይፈታ ህልሜ
ላላገኛት ነውወይ ይሄሁሉ ህልሜ
Instrumental
እንዴት ያስደስታል ፍቅር በህልም
አፍ ገጥሞ ጨዋታ ሲያስለመልም
ጽድቅ ነበር በዛው ቢሉ ጭልም
ምኞት ባጥቢያ ዳኛ ላይታገድ
በህልም አለም ጉዞ በሃሳብ መንገድ
ሌሊት መባከን ይሻል ከአጉል መውደድ
ሀገሯ ወዲያ ማዶ ሀገሯ ወዲያ ማዶ
ሀገሯ ወዲያ ማዶ ናፍቆቷ መጣ ማልዶ
ሀገሯ ወዲያ ማዶ ሀገሯ ወዲያ ማዶ
ሀገሯ ወዲያ ማዶ ናፍቆቷ መጣ ማልዶ
Instrumental
ስጋጃ አንጥፌ ግምጃ ብጋርድ
እንኳን ሊሞቀኝ አለኝ ብርድ ብርድ
ጤዛ ወሮታል የኛውን ሰፈር
ብቻን መኝታ እንደምን ልድፈር
ሌት ፈሌት ለመንገድ ቀን ከመሰወር
ምነው እንደ አጥቢያ ብትወረወር
Instrumental
አይሆንላት ይሆን ከዐይን መሰወሯ
በህልም እንደሸማኔ ፍቅር መደወሯ
የአንድአንዱ ሰው ጥበብ ምኑ ይታወቃል
ቀን እያስቀደሰ ሌሊት ልብ ይሰርቃል
ቀን እያስቀደሰ ሌሊት ልብ ይሰርቃል
ደግሞ መሸ መሸ እስኪላነጣጥፈው
ቀኑን እየባንነኩ ሌሊቱን በሃሳብ ባልፈው
የእንቅልፍ አጀብ ከብዶኝ በሰመመን ስናኝ
በህልሜ ትመጣለች ያቺ የቀን መናኝ
በህልሜ ትመጣለች ያቺ የቀን መናኝ
አሄሄ
ሀገሩ የት ይሆን የዋልሺበት
ታሳድሪ እንደሆን የመሸበት
ጠያይቄ ልምጣ ካለሽበት
በፍቅር እያሰብኳት ከመብሰልሰል
ሌሊት እያሰብኳት ከምደሰት
ነግቶ ባያት ምነው ብትከሰት
ሀገሯ ወዲያ ማዶ ሀገሯ ወዲያ ማዶ
ሀገሯ ወዲያ ማዶ ናፍቆቷ መጣ ማልዶ
ሀገሯ ወዲያ ማዶ ሀገሯ ወዲያ ማዶ
ሀገሯ ወዲያ ማዶ ናፍቆቷ መጣ ማልዶ
Instrumental
አይችሉም እንጂ ብቸኝነቴን
እንደምን ልጣት ፍቅሬን እምነቴን
ባይልላት ነው ወይ ባይልልኝ
እሷ አይቆርጥላት እኔ አይለይልኝ
ከሆድ ላትወጣ አወይ መቸገር
አንጀት ስትበላ የደሃ ነገር
አንጀት ስትበላ የደሃ ነገር
አንጀት ስትበላ የደሃ ነገር
አንጀት ስትበላ የደሃ ነገር
አንጀት ስትበላ
አንጀት ስትበላ
የደሃ ነገር

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists