Nina Girma - Helm Elim lyrics
Artist:
Nina Girma
album: Majete
ድው ድም
ድው ድም
ድም ድም
ልቤ አለ አልረጋም
በፍጥነት ድው ድም
እጅህን ዘርግተህ ስትጠይቀኝ ስም
በውበትህ ፈዝዤ ዝም ዝም ዝም
ድው ድም
ድው ድም
ድም ድም
ልቤ አለ አልረጋም
በፍጥነት ድው ድም
እጅህን ዘርግተህ ስትጠይቀኝ ስም
በውበትህ ፈዝዤ ዝም ዝም ዝም
ህልም እልም ተጫዋችነቴ ጥሎኝ በመስኮት እልም
በአንዴ አንተን ምኞቴ ላይ ጨምሬ እንዳሻኝ ላልም
ነፍሻው አየር እያውለበለበው ቀሚሴን
ነጭ ፈረስ ጋልበን በሰረገላ ታጅበን
ሁሉ በእጅችን ሁሉ በደጃችን
ደማምቀን ስንውል በወርቃማው ቤታችን
በአእዋፍ ዜማ ልዩ ጣዕም
ባይሆን ህልም እልም
መታ ሲረታ
ምስኪኑ ልቤ በአይን ፍቅር ተመታ
ሞገሱን ተጎናፅፎት አምሮ ሲመጣ
የሚሆነው አጣ
መታ ሲረታ
ምስኪኑ ልቤ በአይን ፍቅር ተመታ
ሞገሱን ተጎናፅፎት አምሮ ሲመጣ
የሚሆነው አጣ
♪
ድው ድም
ድው ድም
ድም ድም
ልቤ አለ አልረጋም
በፍጥነት ድው ድም
እጅህን ዘርግተህ ስትጠይቀኝ ስም
በውበትህ ፈዝዤ ዝም ዝም ዝም
ድው ድም
ድው ድም
ድም ድም
ልቤ አለ አልረጋም
በፍጥነት ድው ድም
እጅህን ዘርግተህ ስትጠይቀኝ ስም
በውበትህ ፈዝዤ ዝም ዝም ዝም
ህልም እልም
አይኖቼን ሳልከድን ሳላንቀላፋ ሳልም
በዳመና ተሳፍሬ ከአንተ ጋር ስንጎበኝ አለም
ከከፍታ እይታ እያደርናነቅን ተፈጥሮን
ከኢትዮጵያ ተነስተን ስናካል መላ አፍሪካን
ሽር ሽር ስንል በውሃም በየብሱም
እየተጎራረስን ከአገልግሉም
ፍቅርንም እንደዛው ስናጣጣም
ባይሆን ህልም እልም
መታ ሲረታ
ምስኪኑ ልቤ በአይን ፍቅር ተመታ
ሞገሱን ተጎናፅፎት አምሮ ሲመጣ
የሚሆነው አጣ
መታ ሲረታ
ምስኪኑ ልቤ በአይን ፍቅር ተመታ
ሞገሱን ተጎናፅፎት አምሮ ሲመጣ
የሚሆነው አጣ
♪
ነካ ነካ መታ ቢያረገኝ ነቃሁ
ከሱ ጋር ኮብልዬ ህልሜ ውስጥ በቀረሁ
በምናቤ ተሞሽሬ እንዳየሁ
በአንድ ጊዜ እይታ ይህን ሁሉ ተመኘሁ
ነካ ነካ መታ ቢያረገኝ ነቃሁ
ከሱ ጋር ኮብልዬ ህልሜ ውስጥ በቀረሁ
በምናቤ ተሞሽሬ እንዳየሁ
በአንድ ጊዜ እይታ ይህን ሁሉ ተመኘሁ
መታ ሲረታ
ምስኪኑ ልቤ በአይን ፍቅር ተመታ
ሞገሱን ተጎናፅፎት አምሮ ሲመጣ
የሚሆነው አጣ
መታ ሲረታ
ምስኪኑ ልቤ በአይን ፍቅር ተመታ
ሞገሱን ተጎናፅፎት አምሮ ሲመጣ
የሚሆነው አጣ
ድው ድም
ድው ድም
ድም ድም
ልቤ አለ አልረጋም
በፍጥነት ድው ድም
እጅህን ዘርግተህ ስትጠይቀኝ ስም
በውበትህ ፈዝዤ ዝም ዝም ዝም
ድው ድም
ድው ድም
ድም ድም
ልቤ አለ አልረጋም
በፍጥነት ድው ድም
እጅህን ዘርግተህ ስትጠይቀኝ ስም
በውበትህ ፈዝዤ ዝም ዝም ዝም
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist