Kishore Kumar Hits

Nina Girma - Yaselale Lalo lyrics

Artist: Nina Girma

album: Majete


ያሰላሌ ላሎ
ሁሉ ሳለ ወገኔ
በሀገሬ ማሎ

ሲያውቅበት ጨዋታ
የአንድነት ምሳሌ የደስታ
ዘር አይቆጥር የትውልድ ቦታ
አክባሪ ነው ሰውን በሰውነቱ
ሳበኝ አመለካከቱ
የፍቅር ሸማኔ
የአገር ልጅ ወገኔ ይኸው ከጎኔ
አለ ከጎኔ
ናልኝ ናና
የታደለን መና
የህይወት ሚስጠሩ ፍቅር እንደሆነ አሳየና
ናልኝ ናና
የገባህ አለና
የህይወት ሚስጥሩ ፍቅር እንዲሆን ንገረና
ያሰላሌ ላሎ
ሁሉ ሳለ ወገኔ
በሀገሬ ማሎ
ጥላቻን ስሎ እከሌን ከእከሌ
ያሰላሌ ላሎ
ሁሉ ሳለ ወገኔ
በሀገሬ ማሎ
ጥላቻን ስሎ እከሌን ከእከሌ
ክላ ነው መልሱ ሀገሩን ለጠላ
ክላ አለ ይላል ጥሩ መላ
ክላ መሆን አንዱ ለአንዱ ጥላ
ለወገን ወንድም ከላላ

አቋሙ የሚያረካ
በየትኛውም መስፈርት ብለካ
አመዝኖ ልቤን ቢነካ
ለመውደድ ምቹ
የፍቅር ዘማቹ
ላመነበት ጉዳይ ሟቹ
የሰላም ምሳሌዬ
የሀገር ልጅ ወገኔ ሁን ከጎኔ ሁንልኝ ከጎኔ
ና ልኝ ናና
የታደለን መና
የህይወት ሚስጠሩ ፍቅር እንደሆነ አሳየና
ናልኝ ናና
የገባህ አለና
የህይወት ሚስጥሩ ፍቅር እንዲሆን ንገረና
ያሰላሌ ላሎ
ሁሉ ሳለ ወገኔ
በሀገሬ ማሎ
ጥላቻን ስሎ እከሌን ከእከሌ
ያሰላሌ ላሎ
ሁሉ ሳለ ወገኔ
በሀገሬ ማሎ
ጥላቻን ስሎ እከሌን ከእከሌ
ክላ ነው መልሱ አገሩን ለጠላ
ክላ አለ ይላል ጥሩ መላ
ክላ መሆን እንዱ ለአንዱ ጥላ
ለወገን ወንድም ከላላ
ያሰላሌ ላሎ
ሁሉ ሳለ ወገኔ
በሀገሬ ማሎ
ጥላቻን ስሎ እከሌን ከእከሌ
ያሰላሌ ላሎ
ሁሉ ሳለ ወገኔ
በሀገሬ ማሎ
ጥላቻን ስሎ እከሌን ከእከሌ
ያሰላሌ ላሎ
ሁሉ ሳለ ወገኔ
በሀገሬ ማሎ
ጥላቻን ስሎ እከሌን ከእከሌ
ያሰላሌ ላሎ
ሁሉ ሳለ ወገኔ
በሀገሬ ማሎ
ጥላቻን ስሎ እከሌን ከእከሌ
ክላ ነው መልሱ አገሩን ለጠላ
ክላ አለ ይላል ጥሩ መላ
ክላ መሆን እንዱ ለአንዱ ጥላ
ለወገን ወንድም ከላላ
ክላ ክላ ክላ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists