Kishore Kumar Hits

Nina Girma - Majete lyrics

Artist: Nina Girma

album: Majete


በሀገሬ በማውቀው ትሁፊቴ
በተወረሰው ከአያት ከእነ እቴቴ
ገብቼ ከጓዳ ማጀቴ
የወጉን ልሆን አስሬ አንጀቴ
በማውቀው ትውፊቴ
በተወረሰው ከአያት ከእነ እቴቴ
ገብቼ ከጓዳ ማጀቴ
የወጉን ልሆን አስሬ አንጀቴ
ደስታን ልሰጠው ለባለቤቴ
ሳይጎል ይሆን እንደነበረው ለአባቴ
ተሳክቶልኝ እኔ በቤቴ
ቢለኝ ሟያሽ ልዩ እኮ ነው አንቺ እመቤቴ
በአክብሮት አንገቴን ደፍቼ
የዘመን ለውጥ የጊዜን ለውጥ ረስቼ
መውደድ እና ማፍቀሬን ገልጬ
እንድነግረው ይሻል ለካ አብዛቼ
የእኔማ ጭንቀቴ
በየ አይነቱ መስራቴ
ከጎመን ከሽሮ ከስጋው ከዶሮው ማብላቴ
የሚወደው ሁሉ አይቀርበት ባለቤቴ
የአስቤዛ ወጪ በዝቶ እስኪወጣ ወደ አናቴ
ብሎ አለኝ ይኼም ቢለኝ ደስ
እንጀቴ እንዲደርስ
እቅፍ አርገሽ ስትስሚኝ ነው የልቤ የሚደርስ
የእኔ ፍቅር ህይወቴ ናፍቀኸኝ ስትይ ቤቴ ስደርስ
ከሰማሁ በቂ ነው ምኞቴም እሱ ነው
ከስራ መልስ መንፈሴ እንዲታደስ
በማውቀው ትሁፊቴ
በተወረሰው ከአያት ከእነ እቴቴ
ገብቼ ከጓዳ ማጀቴ
የወጉን ልሆን አስሬ አንጀቴ
በማውቀው ትሁፊቴ
በተወረሰው ከአያት ከእነ እቴቴ
ገብቼ ከጓዳ ማጀቴ
የወጉን ልሆን አስሬ አንጀቴ
በቃሉ ፊት ቆሜ ቃል ገብቼ
በሀዘን በደስታው ላልታይ ተለይቼ
ቀሪ ህይወቱን በፍቅር ሞልቼ
ሰላሙ እንዲበዛ ልጥር ክብርን ሰጥቼ
የምርጫውን ሁሉ አዘጋጅቼ
ደርሶ ማታ በፈገግታ ተሞልቼ
የቃላት ሀይል ተረድቼ
ላሳውቀው ይገባል አብዝቼ
የእኔማ ጭንቀቴ
በየ አይነቱ መስራቴ
ከጎመን ከሽሮ ከስጋው ከዶሮው ማብላቴ
የሚወደው ሁሉ አይቀርበት ባለቤቴ
የአስቤዛ ወጪ በዝቶ እስኪወጣ ወደ አናቴ
ብሎ አለኝ ይሄም ቢለኝ ደስ
እንጀቴ እንዲደርስ
እቅፍ አርገሽ ስትስሚኝ ነው የልቤ የሚደርስ
የእኔ ፍቅር ህይወቴ ናፍቀኸኝ ስትይ ቤቴ ስደርስ
ከሰማሁ በቂ ነው ምኞቴም እሱ ነው
ከስራ መልስ መንፈሴ እንዲታደስ
በማውቀው ትሁፊቴ
በተወረሰው ከአያት ከእነ እቴቴ
ገብቼ ከጓዳ ማጀቴ
የወጉን ልሆን አስሬ አንጀቴ
በማውቀው ትሁፊቴ
በተወረሰው ከአያት ከእነ እቴቴ
ገብቼ ከጓዳ ማጀቴ
የወጉን ልሆን አስሬ አንጀቴ
በማውቀው ትሁፊቴ
በተወረሰው ከአያት ከእነ እቴቴ
ገብቼ ከጓዳ ማጀቴ
የወጉን ልሆን አስሬ አንጀቴ
በማውቀው ትሁፊቴ
በተወረሰው ከአያት ከእነ እቴቴ
ገብቼ ከጓዳ ማጀቴ
የወጉን ልሆን አስሬ አንጀቴ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists