Kishore Kumar Hits

Nina Girma - Mongo lyrics

Artist: Nina Girma

album: Majete


ያሸነፈው ያለፈው
በድል የወጣው
ማንነቱን የተፈታተነው
ጥንካሬ እያለው አድክሞ አቅሙን የነሳው
እስኪያይ ብርሀን ቀን ወቶለን አልፎለት
ቢያሳዝነኝ ረስቶ ማየት ያን ድህነት
መንገዱን ረስቶ ያንን ውጣ ውረድ ልፋት
ሲጎርር አየሁት አብሮ አደጉ ላይ በድፍረት
አይ ድፍርት
ወዯዯ ወዯዯ
ሰው ማንነቱን ሲረሣ አየሁ
ወዯ አይ ወዯ
ስለሆነለት ሳይል እሠየው
ወዯዯ ወዯዯ
ዳግም ማጣትም አለ ሞኞ
ሞኞ አይ ሞኞ
ኋላ እንዳትል ወዯ

ጥሮ ግሮ ያቅሙን ሆኖ የፊቱን ስሎ
ከሚያይ እማ ማንነቱ ቀሎ
ይመርጣል በሰላም ማደርን ተመስገን ብሎ
እስኪያይ ብርሃን ቀን ወቶለት አልፎለት
እጅ አይሰጥም ቢጣበቅበት ድህነት
መንገዱን እስኪያልፉት ይህን ውጣ ውረድ ልፋት
ይጠብቀኝ ብሎ የሰው እጅን ከማየት ከማየት

ወዯዯ ወዯዯ
ሰው ማንነቱን ሲረሣ አየሁ
ወዯ አይ ወዯ
ስለሆነለት ሳይል እሠየው
ወዯዯ ወዯዯ
ዳግም ማጣትም አለ ሞኞ
ሞኞ አይ ሞኞ
ኋላ እንዳትል ወዯ

ቢራራ ምናል ቢራራ
አስቦ የራሱን ጊዜ መከራ
ቢራራ ልቡ ቢራራ
ታውሶት ያ ዘመነ መራራ
ቢራራ ምናል ቢራራ
ሆኖ እንዳልነበረ ኑሮ ተራራ
ቢራራ ልቡ ቢራራ
ለወገኑ ደግሞ ቢደርስ በተራ
ወዯዯ ወዯዯ
ሰው ማንነቱን ሲረሣ አየሁ
ወዯ አይ ወዯ
ስለሆነለት ሳይል እሠየው
ወዯዯ ወዯዯ
ዳግም ማጣትም አለ ሞኞ
ሞኞ አይ ሞኞ
ኋላ እንዳትል ወዯ
ወዯዯ ወዯዯ
ዳግም ማጣትም አለ ሞኞ
ሞኞ አይ ሞኞ
ኋላ እንዳትል ወዯ
ወዯዯ ወዯዯ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists