Kishore Kumar Hits

Nina Girma - Tegabezu lyrics

Artist: Nina Girma

album: Majete


እሰይ
ሲፈቅድልን ሲቀናን
ለዛሬው እለት አበቃን
ሲደመር አንድ ቀን ይኸው ለማየት አነቃን
እሰይ
እድሜ ሰቶን ከጤና
አሜን ይሁን ህይወት የቀና
ከቁጥር ሳንጎል ከአመት አመት ደግሞ ያድርሰና
በሀገር ልብሱ ተውበን
በአዲስ መንፈስ ታጅበን
መዐድ ቀርቦ መሶብ ተከቦ
ወዳጅ በጉርሻ ጠግቦ
ብሩህ ልዮ ቀን ነው የፌሽታ
መልካም ስሜት ቤቱን ሞልታ
ደምቆ እስክስታ በእልልታ እልልታ
ተጋበዙ
ይጣል ዳስም በሬ
ጥጋብ ይሁን ሁሉ አፍርቷል ፍሬ
ብሉ ጠጡ ሽር ጉድ ብዬ
እናክብር ሰብሰብ ብለን ዛሬ
ይጣል ዳስም በሬ
ጥጋብ ይሁን ሁሉ አፍርቷል ፍሬ
ብሉ ጠጡ ሽር ጉድ ብዬ
እናክብር ሰብሰብ ብለን ዛሬ
እሰይ
በዚህ እለተ ሰናይ
ተሰብስበን አንድ ላይ
በፍቅር ታጅበን ሀሴት ሁለችን ፊት ላይ
እሰይ
እንደ ማለዳ ፀሀይ ጮራ
ፈክቶ የሚያበራ
አምረን ደምቀን ተሸቀርቅረን
ስንታይ በጋራ
በሀገር ልብሱ ተውበን
በአዲስ መንፈስ ታጅበን
መዐድ ቀርቦ መሶብ ተከቦ
ወዳጅ በጉርሻ ጠግቦ
ብሩህ ልዮ ቀን ነው የፌሽታ
መልካም ስሜት ቤቱን ሞልታ
ደምቆ እስክስታ በእልልታ እልልታ
ተጋበዙ
ይጣል ዳስም በሬ
ጥጋብ ይሁን ሁሉ አፍርቷል ፍሬ
ብሉ ጠጡ ሽር ጉድ ብዬ
እናክብር ሰብሰብ ብለን ዛሬ
ይጣል ዳስም በሬ
ጥጋብ ይሁን ሁሉ አፍርቷል ፍሬ
ብሉ ጠጡ ሽር ጉድ ብዬ
እናክብር ሰብሰብ ብለን ዛሬ
ተውረግረጊበት አሸነፈች አሸነፋች
የእኛ ልጅ በርቺ እንዳትረቺ
እጅ እንዳትሰጪ
ተውረግረጊበት አሸነፈች አሸነፋች
የእኛ ልጅ በርቺ እንዳትረቺ
እጅ እንዳትሰጪ
ተጋበዙ
ይጣል ዳስም በሬ
ጥጋብ ይሁን ሁሉ አፍርቷል ፍሬ
ብሉ ጠጡ ሽር ጉድ ብዬ
እናክብር ሰብሰብ ብለን ዛሬ
ይጣል ዳስም በሬ
ጥጋብ ይሁን ሁሉ አፍርቷል ፍሬ
ብሉ ጠጡ ሽር ጉድ ብዬ
እናክብር ሰብሰብ ብለን ዛሬ
ይጣል ዳስም በሬ
ጥጋብ ይሁን ሁሉ አፍርቷል ፍሬ
ብሉ ጠጡ ሽር ጉድ ብዬ
እናክብር ሰብሰብ ብለን ዛሬ
ይጣል ዳስም በሬ
ጥጋብ ይሁን ሁሉ አፍርቷል ፍሬ
ብሉ ጠጡ ሽር ጉድ ብዬ
እናክብር ሰብሰብ ብለን ዛሬ
መደሰት ነው ዛሬ
በርቸስቸስ
እዚጋ እዛጋ እዚጋ ቸብ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists