Kishore Kumar Hits

Nina Girma - Msoso lyrics

Artist: Nina Girma

album: Majete


በአንድ ጣራ መጥኖን
ቢሞቅ ቢበርደን
ተቃቅፈን በከሰል ሞቀን
እንዳየሩ ፀባይ ውለንም አድረን
በኮሳሳ ጎጆአችን ሳይከፍን
የእማ ጉያ መጠለያ
ራስን የመቻል ሸክም ሲበዛ መከለያ
የአዋቂነት ሲመጣ ጭንቀት
ሮጠን የምንሄድባት ፍቅር ምስጋና ያንሳል ለእናት
በአንድ ጣራ መጥኖን
ቢሞቅ ቢበርደን
ተቃቅፈን በከሰል ሞቀን
እንዳየሩ ፀባይ ውለንም አድረን
በኮሳሳ ጎጆአችን ሳይከፍን
የጀግንነት ምሳሌዬ አባዬ
የቤታችን ግርማ ሞገሱ ነህ መኩሪያዋ
የጀርባ አጥንት የአንተስ ልፋት
ልጆችህ ደርሰው ለቁምነገር አብቅተህ ለማየት
እማምዬ አብዬ
ፍቅር ውለታቹን ልመልስ እንዴት ብዬ
እማምዬ አብዬ
መውደድ እና አክብሮቴን ላሳይ ጎንበስ ብዬ
እማምዬ አብዬ
ፍቅር ውለታቹን ልመልስ እንዴት ብዬ
እማምዬ አብዬ
መውደድ እና አክብሮቴን ላሳይ ጎንበስ ብዬ
ምኞት አለኝ
እድሜ ጨማምሮ ይስጥልኝ
ዳግም አይገኝ እናት አባት የሚተካ የለም በእውነት
ቢያድለኝ የደስታ ምንጫቹ ቢያረገኝ
እኔም ሰው አርጎኝ ልጡራቹ በኩራትም መርቁኝ
የእማ ጉያ መጠለያ
ራስን የመቻል ሸክም ሲበዛ መከለያ
የአዋቂነት ሲመጣ ጭንቀት
ሮጠን የምንሄድባት ፍቅር ምስጋና ያንሣል ለእናት
የጀግንነት ምሳሌዬ አባዬ
የቤታችን ግርማ ሞገሱ ነህ መኩሪያዋ
የጀርባ አጥንት የአንተስ ልፋት
ልጆችህ ደርሰው ለቁምነገር አብቅተህ ለማየት
እማምዬ አብዬ
ፍቅር ውለታቹን ልመልስ እንዴት ብዬ
እማምዬ እብዬ
መውደድ እና አክብሮቴን ላሳይ ጎንበስ ብዬ
እማምዬ አብዬ
ፍቅር ውለታቹን ልመልስ እንዴት ብዬ
እማምዬ እብዬ
መውደድ እና አክብሮቴን ላሳይ ጎንበስ ብዬ
እማምዬ አብዬ
ፍቅር ውለታቹን ልመልስ እንዴት ብዬ
እማምዬ እብዬ
መውደድ እና አክብሮቴን ላሳይ ጎንበስ ብዬ
እማምዬ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists