Kishore Kumar Hits

Chelina - Birhanun Sai lyrics

Artist: Chelina

album: Chelina, Vol. 1


ጎህ ቀዶ በጠዋት ስነሳ
ሀዘን አድባይ አለ በኔ ጋር
በመስኮቱ ቀዳዳ የብርሀን ጮራ ዘልቆ ክፍሉ ሲገባ
ተገፈፈ ጨለማው
ተለወጠ ደመናው
ብርሀን ሳይ ወደላይ
አብቅቷል የጭንቀቱ ጊዜ
እፎይ አልኩኝ ተስፋን ተሞልቼ
ብርሀን ሳይ ወደላይ
አብቅቷል የጭንቀቱ ጊዜ
እፎይ አልኩኝ ተስፋን ተሞልቼ
ክረምት አልፎ በጋ መጣ
ምድር ደምቃ በአደይ አበባ
ይሸታል በአል በአል
በየ ቤቱ የበአል ቅኝቱ
ተለወጠ ክረምቱ
ተቋረጠ ዝናቡ

ብርሀን ሳይ ወደላይ
አብቅቷል የጭንቀቱ ጊዜ
እፎይ አልኩኝ ተስፋን ተሞልቼ
ብርሀን ብርሀን በራ በጨለማ
በጭንቀት በሀዘን ሳለው በጨለማ
ብርሀን ብርሀን መጣ
ጨለማው አበቃ አአ ብርሀን ሳይ
ወደላይ አብቅቷል የጭንቀቱ ጊዜ
አፎይ አልኩኝ ተስፋ ተሞልቼ
ብርሀኑን ሳይ ወደ ላይ
አብቅቷል የጭንቀቱን ጊዜ
እፍይ አለኩኝ ተስፋ ተሞልቼ
ብርሀኑን ሳይ ወደ ላይ
አብቅቷል የጭንቀቱን ጊዜ
እፍይ አለኩኝ ተስፋ ተሞልቼ
እፎይ! እፎይ! እፎይ!

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists