Kishore Kumar Hits

Chelina - Anemogn lyrics

Artist: Chelina

album: Chelina, Vol. 1


እናት በጣም ተደሰተች
ጀግና ወለድኩ ብላ
የሷን ኑሮ ሁሉ ገታ
ለፋች ቻለች ተዋጋች
ነፃ እንድ'ኖን ብላ
ወደቀች ደሟን አፍሳ
አዝላ፣ ጠርጋ
ሳትጠየፍ አሳድጋ
ግን እኛ
ወድቃ ስናበዛ ምሳር በሷ
ከዚ ሌላ አገር አለን ወይ ኸረ እኛ
ማን አሳሳተን እናት ላይ እንድንይዝ ካራ
ከዚ ሌላ አገር አንሞኝ የለንም እኛ
ማን እንደ አገር ብትሞላ ባትሞላ
የዱር አራዊቱ ሁሉ
እንደ ቤት እንስሳ
ያኔ ማየት ነበር ተራ
በሁሉ ሙሉ በሁሉ ጌታ
እንድ'ኖን ልጆቿ
ወርቅ ሃብቷን አውርሳ
ግን ቀኝ እጅ የግራን
ኪስ ለመስረቅ ሲገባ
እሺ ምን ይባላል
በፍፁም አይገባ
ከዚ ሌላ አገር አለን ወይ ኸረ እኛ
ማን አሳሳተን እናት ላይ እንድንይዝ ካራ
ከዚ ሌላ አገር አንሞኝ የለንም እኛ
ማን እንደ አገር ብትሞላ ባትሞላ
አይይይይይይይ
ውይይይይይይ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists