Kishore Kumar Hits

Chelina - Bati lyrics

Artist: Chelina

album: Chelina, Vol. 1


አጉል ቀረ ልቤ
ኦሆ ሆ ኦሆ ሆ
ከምንም ሳይሆነው
ኦሆ ሆ ኦሆ ሆ
ምክንያት ስደረድር
ፍቅርን ላወዳድር
የትም የማይሄድ መስሎኝ
ምርጫዬን በዝርዝር
አሁን ከየት ላግኘው
ኦሆ ሆ ኦሆ ሆ
አልቻልኩ ልመልሰው
ኦሆ ሆ ኦሆ ሆ
የራስ ውሳኔ የለኝ
ተመራሁ በነርሱ
ቤተሰብ ጓደኛ
መስሎኝ የሚያኖሩ
አውላላ ሜዳ ላይ
ኦሆ ሆ ኦሆ ሆ
እንደቀረሁ ሳየሁ
ልቤ ላልወደደው
እጅ እንዳይሰጥ ኧረ ተው
ኦሆ ሆ ኦሆ ሆ
ቆንጆ እንዳንተ ማነው
ኦሆ ሆ ኦሆ ሆ
ልብን የሚያሳምም
ኦሆ ሆ ኦሆ ሆ
ፈገግታው ልብ ሚሰርቅ
ኦ ኦ ኦሆ ሆ
ዓይንን የሚማርክ
ኦሆ ሆ ኦሆ ሆ
ድንገት ልብህ እዚህ ካለ
ካልሄደ እዚያ ማዶ
ልቤ ታስሯል ባንተ
እርሻ እንዳለ ነዶ
እንዴት አምሮበታል
ኦሆ ሆይ ወይ ጉድ ነው
እንዴት አሸብርቋል
ኦሆ ሆይ ወይ ጉድ ነው
ቃሉ የእውነት ነው
ልብን ያሳርፋል
ካለሱ
ወይ ወይ ወይ ወይ
አለሱማ እንዴት ይዘለቃል
ኦሆ ሆ ኦሆ ሆ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists