Kishore Kumar Hits

Dibekulu - Hilm Mesay lyrics

Artist: Dibekulu

album: Yetu Gar Neh?


ቆንጂት እንዴት ነው ነገሩ
ከአይን ያውጣሽ አልበዛም ማማሩ
ኡ... አንቺ ቆንጆ
ዛሬ ለካ ሲነጋ
ሊያሳየኝ ነው ጉደኛ ሸጋ
ሲርገበገብ ቀኝ አይኔ
መች ታወቀኝ ተዐምር ቀኔ
ዘመናይ አረማመዷ
አውሎ ነው ነፋስ
ሁሉም በአይኑ ሲሸኛት
ከጎኗ እንዴት ልድረስ
ህልም መሳይ ከአይን በላይ
ተአምረኛ በቁንጅና
ህልም መሳይ የማያይዋት
ዳግም በውን እንደገና
(ኦውዎ) እውነት አይመስልም
(ኦውዎ) ውበቷ ዳሩ
(ኦውዎ) እራሴ ባልሆን (ሌላ የማይሆን)
(ኦውዎ) ባይ ምስክሩ
ኡ ኧረ ጉድ ነው
ኡ ኧረ ጉድ ነው
ኡ ኧረረረረ
ኡ ኧረ ጉድ ነው
ኡ ኧረ ጉድ ነው
ኡ ኧረረረረ
ልዩ ቀን ነው የገዴ
የሚከሰት በህይወት አንዴ
ከሰው መሀል ድንገት አልፋ
ጉድ በል ሀገር ዋ ልቤ ጠፋ
ቆንጆ ነች ብሎ መናገር
ማጣጣል ነው (ከንቱ ልፋት)
ውበቷን ገልጦ የሚያስረዳ
ቃላቱ ማን አለው
ህልም መሳይ (ኤ...)
ከአይን በላይ (ኦ...)
ተአምረኛ በቁንጅና (ኤ...)
ህልም መሳይ (ህልም መሳይ)
የማያይዋት (ኦ...)
ዳግም በውን (ዳግም በውን)
እንደገና (እንደገና)
(ኦውዎ) እውነት አይመስልም
(ኦውዎ) ውበቷ ዳሩ
(ኦውዎ) እራሴ ባልሆን (ሌላ የማይሆን)
(ኦውዎ) ባይ ምስክሩ
ኡ ኧረ ጉድ ነው
ኡ ኧረ ጉድ ነው
ኡ ኧረረረረ
ኡ ኧረ ጉድ ነው
ኡ ኧረ ጉድ ነው
ኡ ኧረረረረ
እንትፍ እንትፍ ይላል
ይላል ከአይን ያውጣሽ
የሀገር ሰው እንደ ልጁ
እንደ አይኑ እያየሽ
እንትፍ እንትፍ ይላል
ይላል ከአይን ያውጣሽ
እቱ በአንቺ ጉዳይ
ስንቱን አማከርሽ
(ህልም መሳይ) ተውባለች አሉ
(ከአይን በላይ) ተውባ ተሰርታ
(ተአምረኛ) አለሁ ያለ ሁላ
(በቁንጅና) በእሷ እየተረታ
(ህልም መሳይ) መከረኛው አይኔ
(የማያይዋት) አየና ሙሉ ሰው
(ዳግም በውን) አግባት አግባት አለኝ
ልቤን ወሰወሰው
ኡ ኧረ ጉድ ነው
ኡ ኧረ ጉድ ነው
ኡ ኧረረረረ
ኡ ኧረ ጉድ ነው
ኡ ኧረ ጉድ ነው
ኡ ኧረረረረ
(ኡ ኧረ ጉድ ነው) እንትፍ እንትፍ ይላል
(ኡ ኧረ ጉድ ነው) ይላል ከአይን ያውጣሽ
(ኡ ኧረረረረ) የሀገር ሰው እንደ ልጁ
እንደ አይኑ እያየሽ
(ኡ ኧረ ጉድ ነው) እንትፍ እንትፍ ይላል
(ኡ ኧረ ጉድ ነው) ይላል ከአይን ያውጣሽ
(ኡ ኧረረረረ) የሀገር ሰው እንደ ልጁ
እንደ አይኑ እያየሽ
አንቺ ቆንጆ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists