Kishore Kumar Hits

Dibekulu - Wedet New lyrics

Artist: Dibekulu

album: Yetu Gar Neh?


ወዴት ነው እርካታዬ ምቾቴን ማን ቀማኝ
እየጠጣው ሳለሁ ድንገት እንዴት ጠማኝ
ወዴት ነው ጀግንነት ያሁሉ ፉከራ
በእጄ ጨበጥኩ ያልኩት ሲያበላኝ መከራ

ምንድነው ጉዱ ያለ እቅዱ
ልቤ እንድህ መውደዱ
ማውጣት ማውረዱ
መብረድ መንደዱ በየመንገዱ
ያለ አመሉ ድንገት አካሉ
አጥንቱ መጉደሉ
አወቀ ውስጤ ሰሚኝ አንችዬ
ትተሽ አኩኩሉ
ወዴት ነው እርካታዬ ምቾቴን ማን ቀማኝ
እየጠጣው ሳለሁ ድንገት እንዴት ጠማኝ
ወዴት ነው ጀግንነት ያሁሉ ፉከራ
በእጄ ጨበጥኩ ያልኩት ሲያበላኝ መከራ

መሾም መንገሱ ካባ መልብሱ አይሆን ያለ ዘውዱ
ንጉስ ንግስቱ እንዲህ ነች ለሱ ክብር ቀኝ ክንዱ
እኔም ያላንቺ አይበጅኝ እንጂ ነይ በቀትሩ
ሳይገባ ጀምበር ብትይ ዘንበል ጸናልን መንበሩ
ወዴት ነው እርካታዬ ምቾቴን ማን ቀማኝ
እየጠጣው ሳለሁ ድንገት እንዴት ጠማኝ
ወዴት ነው ጀግንነት ያሁሉ ፉከራ
በእጄ ጨበጥኩ ያልኩት ሲያበላኝ መከራ

ወጣው ወጥተሽ ባይሽ ብዬ
አንቺን ካሉ ጋር ተዳብዬ
ወከክ አልኩኝ አበባዬ
ድንገት ሳይሽ ደርባባዬ
ወጣው ወጥተሽ ባይሽ ብዬ
አንቺን ካሉ ጋር ተዳብዬ
ተርክክ አልኩኝ አበባዬ
እንደው ሳይሽ ደርባባዬ

ጉልህ የጎላ መሻቴ
ብቅ በይ በሞቴ
የኔ አጓጊ ምንዳዬ
አንድ በይ እንግዳዬ
ጉልህ የጎላ መሻቴ
እስቲ በይ በሞቴ
የኔ አጓጊ ምንዳዬ
ሳይመሽ እንግዳዬ
ጉልህ የጎላ መሻቴ
ብቅ በይ በሞቴ
የኔ አጓጊ ምንዳዬ
አንድ በይ እንግዳዬ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists