Kishore Kumar Hits

Dibekulu - Yelibe Zema lyrics

Artist: Dibekulu

album: Yetu Gar Neh?


በፍቅር አለም ካንቺ ጋራ
ስቀርብሽ ደስታን ልጋራ
መውደዴን ከቃሌ አትጠብቂው
ሀቄን በአፍ ላታውቂው
አንቺን ማፍቀሬን አልተርክም
ስሜቴን በቃሌ አልሰብክም
መርምረሽ እወቂው መውደዴን
ተረድተሽ የሆዴን

ሳስብሽ ለኩሼ ሻማ
የፍቅሬን ፉጨት ሳሰማ
ባይደርስም በየከተማው
ግልፅ ነው የልቤ ዜማው
ሳስብሽ ለኩሼ ሻማ
የፍቅሬን ፉጨት ሳሰማ
ባይደርስም በየከተማው
ጥልቅ ነው የልቤ ዜማው

ፍቅሬን ደግሼው እልቤ ላይ
ሆኜልሽ ካላንቺ ማላይ
ስጠራሽ ነይልኝ ከዳሴ
ሳትጠብቂብኝ ውዳሴ
ሀሳብሽ ብልሀት የበዛው
መንፈስሽ ፍቅር የገዛው
ፀባይሽ ሁሉን ያስማማ
አክሱማዊት ነሽ አንቺማ

ሳስብሽ ለኩሼ ሻማ
የፍቅሬን ፉጨት ሳሰማ
ባይደርስም በየከተማው
ግልፅ ነው የልቤ ዜማው
ሳስብሽ ለኩሼ ሻማ
የፍቅሬን ፉጨት ሳሰማ
ባይደርስም በየከተማው
ጥልቅ ነው የልቤ ዜማው

ፍቅራችን ለአመታት ኖሮ
ዘመናትን አስቆጥሮ
ይብቃልን ለብዙ ሻማ
ትዝታን እንድንሻማው
ፍቅራችን ለአመታት ኖሮ
ዘመናትን አስቆጥሮ
ይብቃልን ለብዙ ሻማ
ትዝታን እንድንሻማው
ይብቃልን ለብዙ ሻማ
ትዝታን እንድንሻማው
ይብቃልን ለብዙ ሻማ
ትዝታን እንድንሻማው

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists