Kishore Kumar Hits

Dibekulu - Ney Wedene lyrics

Artist: Dibekulu

album: Yetu Gar Neh?


ኧረ ነይ ኧረ ነይ
ኧረ ነይ ወደ እኔ
ካንቺ ውጪ ላላይ ምያለው ኧረ እኔ
ኧረ ነይ ኧረ ነይ
ኧረ ነይ ወደ እኔ
ከሀገር ልጅ ነው ፍቅር ሌላማ ለምኔ

የሀገሬ ውብ አለም ቆንጆ
አስተዋይ የጨዋ ቁንጮ
ባዳ እንዳታይብኝ ደሞ
ልብሽ ከባህር ማዶ ዘሞ
ነይ ወደ እኔ
ወደ እኔ
ካንቺ ውጪ ማን ለእኔ
የወንዝሽ ልጅ ነኝ ሀገሬን ያልኩኝ
በክፉ ደጉ ጥዬሽ ያልሄድኩኝ
ነይ ወደ እኔ
ወደ እኔ
ካንቺ ውጪ ማን ለእኔ
ኧረ ነይ ኧረ ነይ
ኧረ ነይ ወደ እኔ
ካንቺ ውጪ ላላይ ምያለው ኧረ እኔ
ኧረ ነይ ኧረ ነይ
ኧረ ነይ ወደ እኔ
ከሀገር ልጅ ነው ፍቅር ሌላማ ለምኔ
ዘመናይ ውብ ልበ ሰፊ
አየሩን ባህሩን ቅዘፊ
እንዙር እንጂ ዳር አለሙን
መታሰር በወንዝሽ ለምን
ነይ ወደ እኔ
ወደ እኔ
ካንቺ ውጪ ማን ለእኔ
እጄን ያዢና ልውሰድሽ ማዶ
ብቻዬን አልሂድ ልቤ አንቺን ወዶ
ነይ ወደ እኔ
ወደ እኔ
ካንቺ ውጪ ማን ለእኔ
ኧረ ነይ ኧረ ነይ
ኧረ ነይ ወደ እኔ
ካንቺ ውጪ ላላይ ምያለው ኧረ እኔ
መወለዱም ቋንቋ ነው ፍቅር ነው ድንበሩ
የሄደበት ጋር ሆኗል ሁሉም ሰው ሀገሩ
ነይ ነይ ስልሽ እሺ በይ ግቢልኝ ከእቅፌ
አለምሽን ላሳይሽ ከአድማስሽ አልፌ
ኧረ ነይ ኧረ ነይ
ኧረ ነይ ወደ እኔ
ካንቺ ውጪ ላላይ ምያለው ኧረ እኔ
ኧረ ነይ ኧረ ነይ
ኧረ ነይ ወደ እኔ
ከሀገር ልጅ ነው ፍቅር ሌላማ ለምኔ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists