Kishore Kumar Hits

Dibekulu - Yetsion Werq lyrics

Artist: Dibekulu

album: Yetu Gar Neh?


ምርጧ የፅዮን ወርቅ የወጣሽ ከግዮን
ምድራችን ያፈራሽ የኛ እንቆጳዝዮን
የዘወትር ደስታን ሳታይው ባንቺ ውበት
ሳይደላሽ ይጠራል ገፅሽ ከመስታወት
ይግባኝ ባይሉበት በመልክ አሰጣጡ
ይገረሙብሻል ከአለም የሚመጡ
ወጥተሽ እማ ቢያዩሽ ካደግሽበት ጎጆ
አልፈጠረም ባሉ እንዳንቺ አይነት ቆንጆ
ሁሌም ኢትዮጵያ ለኔ
ውዴ ፅድቄ ጽዮኔ
ምድሬ ሀገር ገነቴ
ሃቄ ፍቅር እምነቴ
ሁሌም ኢትዮጵያ ለኔ
ውዴ ፅድቄ ጽዮኔ
ምድሬ ሀገር ገነቴ
ሃቄ ፍቅር እምነቴ

የገነባው ህንፃ ሞገሱ የጎላ
ማን ሰራ እንደ አባትሽ እንደ ላሊበላ
ጥበብን ያሳዩት በአክሱም አደባባይ
ዛሬም ያንቺ አያቶች ይኮራሉ በአባይ
የሊቆች ፍሬ ነሽ የአበው የትላንቱ
ተአምር ትሰሪያለሽ አንቺም እንደጥንቱ
የፋሲል ማደሪያው የቆመው በጎንደር
የሃረርጌ ግንቡ ታጥቶለታል ወደር
ምስሌ የኢትዮጵያዬ
ክብሬ ነሽ እንቆጳዬ
የእኔን አክብሮት እንቺ
ሁሌም ኩሩ ነኝ ባንቺ
ምስሌ የኢትዮጵያዬ
ክብሬ ነሽ እንቆጳዬ
የእኔን አክብሮት እንቺ
ሁሌም ኩሩ ነኝ ባንቺ

ምስሌ የኢትዮጵያዬ
ክብሬ ነሽ እንቆጳዬ
የእኔን አክብሮት እንቺ
ሁሌም ኩሩ ነኝ ባንቺ
ምስሌ የኢትዮጵያዬ
ክብሬ ነሽ እንቆጳዬ
የእኔን አክብሮት እንቺ
ሁሌም ኩሩ ነኝ ባንቺ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists