Kishore Kumar Hits

Dibekulu - Lidresish lyrics

Artist: Dibekulu

album: Yetu Gar Neh?


ልድረስሽ እንደ ግጥም ላፍልቅሽ እንደ ዜማ
አለም አጀብ ያለው ፍፁም ያልተሰማ
እንደ አእዋፋት ቃና ጆሮ የሚሰማማ
እንደ ጣና ደንገል ውብ ባለ ግርማ
በቀና የልብሽ ጎዳና
ነውና ድብቅ ገናና
አንቺ ከአውድማው እኔ ከአምባው ላይ
ክራር ስደረድር ተከፍቶ ሰማይ
ቀለማትን ረጨ ስለኛ ጉዳይ
ከእርሱ የተቸርሽኝ የምድሩ ነዋይ
በቀና የልብሽ ጎዳና
ነውና ድብቅ ገናና
በቀና የልብሽ ጎዳና
ነውና ድብቅ ገናና
ከሀቀኞቹ ቁና ጎርፈሽ እንደ ጅረት
በታላቅ ወደቀ የሸንጋይ መሰረት
አወይ ትህትናሽ ምሉዕ ያለወረት
ሲያወጉት መሰለ የብልሃት ተረት
አወይ ትህትናሽ ምሉዕ ያለወረት
ሲያወጉት መሰለ የብልሃት ተረት

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists