Kishore Kumar Hits

Melat kelemework - Taytu Bilo lyrics

Artist: Melat kelemework

album: Ende Maleda


ንጉስ አደረግሽኝ እቴ
ሆነሽኝ ብርታቴ
ጣይቱ ነው ሚመጥንሽ
ለኔ የምጠራሽ
ይለኛል ዉዴ ሲጠራኝ
ስያሜ አጠረኝ
ሚጠራኝ በስሜ መች ሆኖ
ይላል ቃል መጥኖ
ጣይቱ ብሎ ጣይቱ ጣይቱ ነው ጣይቱ ብሎ
ስሜን ሰየመው ጣይቱ ጣይቱ ነው ጣይቱ ብሎ
ፍቅሩን አክሎ
ጣይቱ ብሎ ጣይቱ ጣይቱ ነው ጣይቱ ብሎ
አፀደቀልኝ ጣይቱ ጣይቱ
መጠሪያዬ አደጎ
ከጠያይሞቿ አፈር ምድር
ቢታይ የታሪኩ ማህደር
ለነፃነት ጀንበር
ዱሉን እንዲቀዳጅ ከሓላ
ባሏን በርታ አለሁኝ ብላ
ብልሃት አቀብላ
ለአምላኻ ተስላ ድሉ ሆነ ድሏ
ለጥቁር ህዝብ ሆን ጥላ
በዚች አገር ዋርካ
ነው ሚጠራኝ ለካ
ሳውቀው ልቤ ተመካ
ጣይቱ ብሎ ጣይቱ ጣይቱ ነው ጣይቱ ብሎ
ስሜን ሰየመው ጣይቱ ጣይቱ ነው ጣይቱ ብሎ
ፍቅሩን አክሎ
ጣይቱ ብሎ ጣይቱ ጣይቱ ነው ጣይቱ ብሎ
አፀደቀልኝ ጣይቱ ጣይቱ
መጠሪያዬ አደጎ
ከጠንካራ ወንድ ጀርባ አለች
ለባሏ መክታ የሆነች
ይሉትን ያሳየች
እንደሷ መሆኑን ተመኝው
ልቧን በሚወደኝ ውስጥ አየው
ፍቅር እውነቱን ለየው
እቴጌ ነኝና እሱም የቤቴ አፄ
የራስ ዘውዱ መልኩ ገፄ
በህይወት ጦርነት
ፊት ልሰለፍለት
ቃል በልቤ ገባሁለት
ጣይቱ ብሎ ጣይቱ ጣይቱ ነው ጣይቱ ብሎ
ስሜን ሰየመው ጣይቱ ጣይቱ ነው ጣይቱ ብሎ
ፍቅሩን አክሎ
ጣይቱ ብሎ ጣይቱ ጣይቱ ነው ጣይቱ ብሎ
አፀደቀልኝ ጣይቱ ጣይቱ
መጠሪያዬ አደጎ
የሰጠኝ ስያሜ ልቤን ሆነ ረቺ
ጀግኝ ጀግን አለኝ በርቺ ተበራቺ
መንፈስ ምታስቀና ጊዜ አይሽሬ መሪ
ምግባሯ አደራ ነው ገድል ጀብዷአኩሪ
ሰመ መልካም መሆን ዘመን ቢቀያየር
ይነሳል ይወሳል ይወራል እያደር
ጣይቱ ብሎ ጣይቱ ጣይቱ ነው ጣይቱ ብሎ
ስሜን ሰየመው ጣይቱ ጣይቱ ነው ጣይቱ ብሎ
ፍቅሩን አክሎ
ጣይቱ ብሎ ጣይቱ ጣይቱ ነው ጣይቱ ብሎ
አፀደቀልኝ ጣይቱ ጣይቱ
መጠሪያዬ አደጎ
ጣይቱ ብሎ ጣይቱ ጣይቱ ነው ጣይቱ ብሎ
ስሜን ሰየመው ጣይቱ ጣይቱ ነው ጣይቱ ብሎ
ፍቅሩን አክሎ
ጣይቱ ብሎ ጣይቱ ጣይቱ ነው ጣይቱ ብሎ
አፀደቀልኝ ጣይቱ ጣይቱ
መጠሪያዬ አደጎ
ጣይቱ ጣይቱ ጣይቱ ጣይቱ ጣይቱ ጣይቱ
ጣይቱ ጣይቱ ጣይቱ ጣይቱ ጣይቱ ጣይቱ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists