Kishore Kumar Hits

Melat kelemework - Leyelegn lyrics

Artist: Melat kelemework

album: Ende Maleda


እንዃንስ ከሰው ልጅ ከሰራዊት
ከድር ከገደሉም አራዊት
መኖር ትችላለህ ተላምደህ
በፍቅር በሰላም ተስማምተህ
ቅን ልብህ ብርሀን
ተሞልቶበታል እህ
መልካምነትህን
ፊትህ ይናገራል
ለየልኝ ከቀረብኩህ ወዲያ
ለየልኝ ሳውቅህ በይበልጥ
ለየልኝ የወደደህ ልቤ
ለየልኝ ፍቅር ባሰበት
መስህብ አለው ውብ አመልህ ከቁንጅናህ በላይ
ነገሮችህ የእውነት ናቸው አይደለህ አሰመሳይ
እንደ ህፃን ልጅ ልብህ
ፍቅር እንጂ ሽር አያውቅ
ደግ ሰራ ደግ ውለታ ተዘርዝሮ አያልቅ
ለየልኝ ከቀረብኩህ ወዲያ
ለየልኝ ሳውቅህ በይበልጥ
ለየልኝ የወደደህ ልቤ
ለየልኝ ፍቅር ባሰበት
እንዃንስ ከሰው ልጅ ከሰራዊት
ከድር ከገደሉም አራዊት
መኖር ትችላለህ ተላምደህ
በፍቅር በሰላም ተስማምተህ
ቅን ልብህ ብርሀን
ተሞልቶበታል እህ
መልካምነትህን
ፊትህ ይናገራል
ለየልኝ ከቀረብኩህ ወዲያ
ለየልኝ ሳውቅህ በይበልጥ
ለየልኝ የወደደህ ልቤ
ለየልኝ ፍቅር ባሰበት
ቢብስ እንጂ ቢጨምር
ከትላንቱ በላይ የምትሰጠኝ ፍቅር ክብር
አንዱም ሲጎል አላይ
አበባዬ ልክ እንደንብ
ነጋ ጠባ ልቅሰምህ
ይጋባብኝ ቅንነትህ
እውቀት ሁነኝ ልማርህ
በምን ቃላት በምን ቛንቛ ልግለፅ ላብራራ
ደግነትህን ቅንነትህን ሰርክ አያባራ
ለየልኝ ከቀረብኩህ ወዲያ
ለየልኝ ሳውቅህ በይበልጥ
ለየልኝ የወደደህ ልቤ
ለየልኝ ፍቅር ባሰበት
ካንተ ጋር ለመኖር
ለየልኝ በቃ ወስኛለው
ለየልኝ በቅን ልብህ ፍቅር
ለየልኝ ተይዤልሀለው

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists