Exodus Getahun - Ewedhalew lyrics
Artist:
Exodus Getahun
album: Eyayehu
አይኔን አንስቻለሁ ከወዲህ ከወዲያ
አንተን ብቻ ማየት ይሁን የኔ ምርጫ
ሌላው ነገር ቀርቶ ልብ የሚያባዝነው
ሃሳቤ መንፈሴ ትኩረቴ አንተ ላይ ነው አንተ ላይ ነው
አይኔን አንስቻለሁ ተሰፋ ካደረግኩት
አንተን ብቻ ላይህ በጽናት በእምነት
ሌላው ሲቀር ይቅር ልብን የሚያዝለው
ሃሳቤ መንፈሴ ትኩረቴ አንተ ላይ ነው አንተ ላይ ነው
የሱሴ ምርጫዬ ክንፍህ የሸሸገኝ አምባ መጠጊያዬ
የደስታዬ ምክንያት የስኬቴ ሁሉ ምንጭ መድመቂያ ካባዬ
የዛሬ የነገ የዘለዓለም ተስፋ መሪ ለመንገዴ
አለቴ አንተ ነህ ጽኑ መደገፊያ ጉልበቴ ብርታቴ
አይኔን አንስቻለሁ ከሚታየው በላይ
ሁኔታዬን ጥሼ ኢየሱስ አንተን ላይ
ሌላው ሲቀር ይቅር መንፈስ የሚያዝለው
ሃሳቤ ጥማቴ ትኩረቴ አንተ ላይ ነው አንተ ላይ ነው
የሱሴ ምርጫዬ ክንፍህ የሸሸገኝ አምባ መጠጊያዬ
የደስታዬ ምክንያት የስኬቴ ሁሉ ምንጭ መድመቂያ ካባዬ
የዛሬ የነገ የዘለዓለም ተስፋ መሪ ለመንገዴ
አለቴ አንተ ነህ ጽኑ መደገፊያ ጉልበቴ ብርታቴ
በሃዘን በደስታ እጠራሃለሁ እፈልግሃለሁ
ኢየሱስ ጌታዬ ካንተ ወዴት ኦ ወዴት እሄዳለሁ
ስምህን ሁልጊዜ እባርካለሁ እወድሳለሁ
ከሁሉ አስበልጬ መርጬሃለሁ እወድሃለሁ
ኢየሱስ እወድሃለሁ
አባቴ እወድሃለሁ
ጌታ እወድሃለሁ
አዎ እወድሃለሁ
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist