Kishore Kumar Hits

Exodus Getahun - Des Yibelachihu lyrics

Artist: Exodus Getahun

album: Eyayehu


ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ
ደግሜ እላለሁ ደስ ይበላችሁ
ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ
ደግሜ እላለሁ ደስ ይበላችሁ
ጌታ ቅርብ ነው ሰላም የሚሰጥ ለመንፈሳችሁ
የሚያበረታ የሚጠግን ስብራታችሁን
የሱስ ቅርብ ነው እረፍት የሚሰጥ ለመንፈሳችሁ
የሚያሰማራ በመልካሙ መስክ የሚመራችሁ
ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ ደግሜ እላለሁ ደስ ይበላችሁ
በኢየሱስ ደስ ይበላችሁ እርሱን በማወቅ ደስ ይበላችሁ
በሞት ሸለቆ ህይወት ሚቀጥል አጥንት ገጥሞ
ዝናብ ሳይታይ ደመና ሳይኖር ሞልቶ ሸለቆ
እንዴት ይሆናል እግዜር በሰማይ መስኮትን ቢያደርግ
ከቶ አይባልም እጅ አያጥረውም ሲሰራ ሲያበጅ
ደስ ይበላችሁ
እንዴት ደስ ይለኛል
ያ የለፋሁበት እንዲሁ መና ቀርቷል
እንዴት ደስ ይለኛል
ተስፋ ያደረኩት አይታመን ሆኗል
እንዴት ደስ ይለኛል
ሃጢአቴ ተጭኖኝ ድካሜ አይሏል
አትበይኝ ነፍሴ
ረዳቴ ከወዴት ከወዴት ይገኛል
አይንሽን አንሺ ወደ ላይ ኦ ነፍሴ ሆይ
ረድኤትሽ አለ በሰማይ
ኃጢአትሽን ይቅር የሚል የሚፈውስ ህመምሽን
የሰራሽ ጉድለትሽን የሚያውቅ
ለዘለዓለም የማይቆጣ
ህይወትሽንም ከጥፋት የሚከልል በምህረት
ደስ ይበልሽ
አይንህን አንሳ ወደ ላይ ትካዜህን ጣል መስቀሉ ላይ
በአመድ ፈንታ አክሊልን በልቅሶውም የደስታን ዘይት
የምስጋናን መጎናጸፊያ ደርቦልህ የክብር ካባ
ይፈጽመው ዘንድ ይተጋል እግዚአብሔር ይህን ተናግሯል
ደስ ይበልህ
ደስ ይበላችሁ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists