Kishore Kumar Hits

Exodus Getahun - Yekalat Fichi lyrics

Artist: Exodus Getahun

album: Eyayehu


ግርማ ሚለውን ቃል ውስጤ ሲመዝነው
እጅግ የተፈራ የማውቀው አንተን ነው
ብርታትስ ምንድነው እያልኩኝ በልቤ
የብርቱዎች ብርቱ አየሁ ከአጠገቤ
ልቀት ቢሉኝ ቃሉ ትርጉሙ ይጠፋኛል
ኢየሱሴ ከማንም ከምንም ልቀህ ታይተኸኛል
የቃላት ፍቺ ነህ ትርጉም የምትሰጥ
ዘወትር ብትታሰብ ህይወትን ምትመስጥ
በጥበብህ ምስጢር በዕውቀትህ ቀመር
በዝንተ ዓለም ስሌት የማትመረመር
በቅዱስ መጽሐፍህ ጣፍጦ የተጻፈው
ትንቢት ቢሉት ታሪክ በቃልህ ያረፈው
በሠዎች አዕምሮ በፍጥረታት ምናብ
ፍጹም ማይለካ ሌተ ቀን ቢታሰብ
በአንተ መንፈስ ግን ያ ቅኔ ሲፈታ
ኢየሱሴ ስላንተ ብቻ ነው የኔ ድንቅ ጌታ
የመጽሐፍቱ ፍቺ አንተው ነህ የሱሴ
በጉያህ ስትኖር ጠቢብ ሆነች ነፍሴ
ኤልሻዳይ እያለ ከንፈሬ ሲናገር
ተግልጦ ይታየኛል የረቀቀው ነገር
የቃላት ፍቺ ነህ ትርጉም የምትሰጥ
ዘወትር ብትታሰብ ህይወትን ምትመስጥ
በጥበብህ ምስጢር በዕውቀትህ ቀመር
በዝንተ ዓለም ስሌት የማትመረመር

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists