Exodus Getahun - Wede Eyesus lyrics
Artist:
Exodus Getahun
album: Eyayehu
ወደ ሰው ልጆች እግዚአብሔር አየ
ጻድቅ ፍለጋ ተመለከተ
ግን እጁን ያዘው ሃጢአት በመሃል
ሸፈነበት ሰወረው ፊቱን
አንድ ቢታጣ እርሱን ሚፈልግ
እምነት ቢጠፋ ኃጢአት ቢነግስ
የገዛ ክንዱ መድሃኒት ሆነው
እኛን ለማዳን ፍቅር አወረደው
ለእኛ ሞቶ ሃጢአትን ዋጠ
ሰውን ከራሱ ጋር አስታረቀ
በጨለማው ላይ ብርሃን በራ
እኛም መዳን ቻልን በእርሱ ሥራ
የእግዚአብሔር ልጅ ያድናል
የእግዚአብሔር ልጅ
ስሙ ሲጠራ ያድናል
አንዱ ኢየሱስ
መዳን በሌላ በማንም የለም
እንድንበት ዘንድ በተሰጠን ስም
በኢየሱስ ብቻ በቃል በሥራ
መዳን ይሆና ስሙ ሲጠራ
የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ
ሊቀ ካህናችን የእግዚአብሔር በግ
የሚያበራ የንጋት ኮኮብ
የማዕዘን ራስ ነው ኢየሱስ
ሰዎችን ሁሉ የሚያድን
በስጋ የመጣ የእግዚአብሔር ክንድ
ድንቅ መካር ሃያል አምላክ
የዘለዓለም አባት ነው ኢየሱስ
የእግዚአብሔር ልጅ ያድናል
የእግዚአብሔር ልጅ
ስሙ ሲጠራ ያድናል
አንዱ ኢየሱስ
አሁንስ ለምን ትዘገያለህ
ተነስ ስሙን እየጠራህ ተጠመቅ
ከሃጢአትህ ታጠብ
እርሱ እውነት መንገድ ህይወት ነውና
በልጁ የሚያምን አያፍርምና
ና ወደ ኢየሱስ ና
አሁንስ ለምን ትዘገያለህ
ተነስ ስሙን እየጠራህ ተጠመቅ
ከሃጢአትህ ታጠብ
እርሱ እውነት መንገድ ህይወት ነውና
በኢየሱስ የሚያምን አያፍርምና
ና ወደ አባትህ ና
ና ወደ ጌታ ና
ና ወደ ኢየሱስ ና
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist