Kishore Kumar Hits

Exodus Getahun - Fikrh Beza lyrics

Artist: Exodus Getahun

album: Eyayehu


ሳስብ ሳሰላስል
እንዴት እንዴት እንደወደድከኝ
እንዴት እንዴትስ ያለ ዋጋ
እንደከፈልክልኝ
የበጎነት የፍቅር ጥግ መጨረሻ
ነፍስህን ስትሰጥ ለኔ ቤዛ
ሳሰላስል
እንዴት እንዴት እንደመረጥከኝ
እንዴት ባለ ዋጋ እንደዋጀኸኝ
የበጎነት የመልካምነት መጨረሻ
ነፍስህን ስትሰጥ ለኔ ቤዛ ቤዛ ቤዛ
እየተገረፍክ
እየደማህ
ተሰቃየህ
ለኔ ቤዛ
ተተፋብህ
ተሳቀብህ
ተንገላታህ
ሆነህ ጌታ
ምን አይነት ፍቅር ነው
በርባን ተፈታ ከእስር በምህረት
በደም በሃጢአት ከጨቀየበት
የእኔን የእርሱን የሁላችንን
ኢየሱስ ወስዶት ደዌአችንን
በርባን ተፈታ ጌታ ተክቶት
በደሉን ወስዶ ሞቱን ሞቶለት
እንዴት በማይባል ግሩም ፍቅር
ተቀየረ ውርደት በክብር
ምኔን አይተህ ወደድክልኝ
በምን መስፈርት ተመረጥኩኝ
ከጽድቅ የራቅኩ የቁጣ ልጅ
ሳለሁ ፈቅደህ የሞትክልኝ
ምን አይነት ፍቅር ነው
ፍቅርህ በዛ ፍጹም ከአዕምሮዬ
በላይ ነው አልችልም ቆጥሬ
ፍቅርህ በዛ ፍጹም ከአዕምሮዬ
በላይ ነው አልጨርስ ተርኬ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists