Tsega Tesfaye - Yimetal lyrics
Artist:
Tsega Tesfaye
album: Tsadik
ይመጣል
መለከት ይሰማል በቀኑ መጨረሻ
በብዙ የናፈቅነው የረፍታችን አርማ
ሰራዊቱን ይዞ ይመጣል ንጉስ
ለፍርድ ጊዜው ሆኖ
የምድር ኑሮ ሊያበቃ ጊዜው ደርሶልን
ሊገለጥ በክብር ልናየው የሱስን
ይመጣል በመላእክት ታጅቦ ሀሌሉያ
በተስፋ እንጠብቅ ያንን ቀን
የወጉት ሁሉ ያዩታል ጌታችንን በክብር
በደመና ሲመጣ ዋይ ልትል ምድር
አለማቱ ፀጥ ሊሉ ሙታን ለፍርድ ሊቀርቡ
ህያዋኑ ለእሱ የኖሩ የክብር አክሊል ሊቀበሉ
አዲስ ሰማይ ልናይ
አዲስ ምድርን ልናይ
እንደተስፋው ቃሉ ያለውን ይፈፅማል
እናየዋለን እውን ነው ምፅዓቱ
እናየዋለን እውን ነው ምፅዓቱ
ይመጣል በመላእክት ታጅቦ ሀሌሉያ
በተስፋ እንጠብቅ ያንን ቀን
የወጉት ሁሉ ያዩታል ጌታችንን በክብር
በደመና ሲመጣ ዋይ ልትል ምድር
ምጥ እንደማይመጣ ቀጠሮ አሲዞ
ሌባ እንደማይሰርቅ ተዘጋጁ ብሎ
የጌታ ቀን ቀርቧል ይመጣል በድንገት
ይመጣል በድንገት
በምድር በመጠን እንኑር
እናከማች ለሰማይ ቤት
ለማይፈርሰው መኖሪያችን
ምጥ እንደማይመጣ ቀጠሮ አሲዞ
ሌባ እንደማይሰርቅ ተዘጋጁ ብሎ
የጌታ ቀን ቀርቧል ይመጣል ድንገት
ይመጣል በድንገት
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist