Kishore Kumar Hits

Tsega Tesfaye - Deginetih lyrics

Artist: Tsega Tesfaye

album: Tsadik


ደግነትህ
ፍቅር ግድ ብሎህ ከሰማይ ወርደሀል
የደም ላብ አልቦህ መርገሜን ወስደሀል
መናቅ መገፋትን ስለእኔ ተቀበልክ
አካላትክ ደቆ በመስቀል ላይ ዋልክ
ማይነጥፍ ቸርነት ማያልቅ የዋኃት
ደግንትህ እልፍ ነው አንተ ሩህሩህ አባት
ማይነጥፍ ቸርነት ማያልቅ የዋኃት
ደግንትህ እልፍ ነው አንተ ሩህሩህ አባት
እስከሞት ታዘዝህ ለክብርህ ሳትሳሳ
ደምህን ገብረህ ያዝከኝ በውድ ዋጋ
በተድላ እና ነዋይ አይተመን ፍቅርህ
ሞትህ ለህይወት ሆነኝ ምንድነው ምከፍልህ
ማይነጥፍ ቸርነት ማያልቅ የዋሀት
ደግነትህ እልፍ ነው አንተ ሩህሩህ አባት
ማይነጥፍ ቸርነት ማያልቅ የዋሀት
ደግነትህ እልፍ ነው አንተ ሩህሩህ አባት

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists