Kishore Kumar Hits

Feven Yoseph - Tizita lyrics

Artist: Feven Yoseph

album: Chanting Soul


ትዝታ ትዝ ሲል
ትዝ የሚል ትዝ ይላል
የረጋውን ልቤን በስሜት ቆስቁሶ
ማዕበል ያስነሳል
ትዝታ ትዝ ሲል
ትዝ የሚል ትዝ ይላል
የረጋውን ልቤን በስሜት ቆስቁሶ
ማዕበል ያስነሳል
ትዝታ ክንፍ አለው
ጀልባ አለው
በራሪ ቀዛፊ
በጥልቅ ወደኋላ
ከዛሬ አሸፍቶ
ነገን አዘንግቶ
ሚያደርስ ትናንትና
የትዝታ ስሜት ስበቱ ግለቱ
ከገደብ ካለፈ በቁም የሚያስተኛ
በምናብ የሚያስኬድ
ብክንክን የሚያደርግ
ቅዠት ነው ሕልም አለም
በትዝታ ጉልበት ስበት መንገላታት
ነፍስን ያደክማታል
የትዝታ ነገር ትናንትን ዛሬ ላይ
ነገ ላይ የዛሬን
ሁሌ ነው የኋሊት
ትዝታ ክንፍ አለው
ጀልባ አለው
በራሪ ቀዛፊ
በጥልቅ ወደኋላ
ከዛሬ አሸፍቶ
ነገን አዘንግቶ
ሚያደርስ ትናንትና
የትዝታ ስሜት ስበቱ ግለቱ
ከገደብ ካለፈ በቁም የሚያስተኛ
በምናብ የሚያስኬድ
ብክንክን የሚያደርግ
ቅዠት ነው ሕልም አለም
በትዝታ ጉልበት ስበት መንገላታት
ነፍስን ያደክማታል
የትዝታ ነገር ትናንትን ዛሬ ላይ
ነገ ላይ የዛሬን
ሁሌ ነው የኋሊት

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists