መች ይመጣል ቢሉ አላምናቸው
አልዝል አልቦዝን በናፍቆት
ወይም ስሄ ወይም ሲመጣ
እስከማየው እስካገኘው
እንደሞተ ሆኜ ደሞ እንደሚኖር እሰራለሁ
በየእለቱ ሞቼ ዘላለም በእርሱ እኖራለው
ሞትን በሞቱ በሻረው በሱ ሞትም ፈውስ ነው
ወይም ስሄ ወይም ሲመጣ
እስከማየው ማራናታ ናናናና እላለሁ
እንዴት ግሩም ቀን ነው
ጌታን የማይበት
ከዚች አለም ስቃይ
ከቶ የማርፍበት
እየሱስ ሲመጣ
ታጂቦ በክብር
አብረን እንሄዳለን
ልንኖር ከእርሱ ጋር
አንድ ቀን አምላኬን እገናኘዋለሁ
ሚያየኝን ጌታ በአይኔ አየዋለሁ
ከደመናት ከፍ ካለው በላይ እሄዳለሁ
ዘላለም ከእርሱጋ እኖራለሁ
አብረን እንሄዳለን
አብረን እንሄዳለን
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist