Kishore Kumar Hits

Mesfin Mamo - Niges lyrics

Artist: Mesfin Mamo

album: Niges


ከሰው ልጆች ይልቅ ውበትህ እጅግ ያምራል
ሞገስ በከንፈርህ ጌታዬ ይፈሳል
ኢየሱስ ሆይ ዙፋንህ ለዘለዓለም ነው
የመንግሥትህ በትር የቅንነት ነው
የደስታ ዘይትን ከሰማይ ተቀባህ
ለእኔ መዳን ሲባል ከአርያም ተለየህ
የደስታ ዘይትን ከሰማይ ተቀባህ
ለእኔ መዳን ሲባል ከአርያም ተለየህ
ንገሥ ንገሥ አለች ነፍሴ
ክበር ክበር አለች ነፍሴ
ልስገድ ልስገድ አለች ነፍሴ
ኢየሱስ አንተ ነህ ንጉሤ
ተወግዶልኛል ሃፍረቴ
ተመልሶልኛል ውበቴ
ኢየሱስ አንተ ንጉሤ
ሕይወቴ መድኃኒቴ
ስለዚህም ነፍሴን እንዲህ በይ እላታለሁ
ለንጉሡ ክብር ተሸላልሜአለሁ
በወርቅ ልብሶችም ተሸፋፍኛለሁ
ሙሽሪት እሆን ዘንድ ከጎኑ ቆሜአለሁ
ደግሞም እላታለሁ ድህነትን እርሺ
ንጉሡ ወዶሻል እርሱ ነው ጌታሽ
እይ ባባቱ ዘንድ አንቺን ሲያከብርሽ
ልቡን ሁሉ ከፍቶ ምስጢር ሲነግርሽ
የትም የማይገኝ ሙሽራ ነው ኢየሱስ
ስለዚህ በልብሽ ይገባዋል መንገሥ
ንገሥ ንገሥ አለች ነፍሴ
ክበር ክበር አለች ነፍሴ
ልስገድ ልስገድ አለች ነፍሴ
ኢየሱስ አንተ ነህ ንጉሤ
ተወግዶልኛል ሃፍረቴ
ተመልሶልኛል ውበቴ
ኢየሱስ አንተ ንጉሤ
ሕይወቴ መድኃኒቴ
እርሱ ሲመጣልች ለራሱ አልሰሰተም
ክብር አለኝ ብሎ ወደኋላ አላለም
ውርደትሽ ውርደቱ አርጎ ተቀብሎ
አለማመርሽን እንደ ውበት አርጎ
ወዶ ተቀበለሽ እንድትቀበይው
እስቲ በሁሉም ላይ ንገሥ ንገሥ በይው
ወዶ ተቀበለሽ እንድትቀበይው
እስቲ በሁሉም ላይ ንገሥ ንገሥ በይው
ንገሥ ንገሥ አለች ነፍሴ
ክበር ክበር አለች ነፍሴ
ልስገድ ልስገድ አለች ነፍሴ
ኢየሱስ አንተ ነህ ንጉሤ
ተወግዶልኛል ሃፍረቴ
ተመልሶልኛል ውበቴ
ኢየሱስ አንተ ንጉሤ
ሕይወቴ መድኃኒቴ
ንገሥ ንገሥ አለች ነፍሴ
ክበር ክበር አለች ነፍሴ
ልስገድ ልስገድ አለች ነፍሴ
ኢየሱስ አንተ ነህ ንጉሤ
ተወግዶልኛል ሃፍረቴ
ተመልሶልኛል ውበቴ
ኢየሱስ አንተ ንጉሤ
ሕይወቴ መድኃኒቴ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists